ቁርአንን ቅሩ! እርሱ የትንሳኤ ቀን ለባለቤቶቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል።

ቁርአንን ቅሩ! እርሱ የትንሳኤ ቀን ለባለቤቶቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል።

ከአቡ ኡማመተል ባሂሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ "ቁርአንን ቅሩ! እርሱ የትንሳኤ ቀን ለባለቤቶቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል። ሁለቱን አብሪ የሆኑ ምዕራፎች ሱረቱል በቀራንና አሉ ዒምራንን ቅሩ። እነርሱ የትንሳኤ ቀን ልክ ደመና ወይም ጥላ መስለው ወይም ተጠባብቀው ረድፍ የሰሩ የወፎች ሁለት መንጋ መስለው ይመጣሉ። ለባለቤቶቻቸውም ይሟገታሉ። የበቀራን ምዕራፍ ቅሩ! እርሷን መያዝ በረከት ነው። እርሷን መተው ደግሞ የሚያስቆጭ ነው። ደጋሚዎችም አይችሏትም።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን አዘውትሮ በመቅራት ላይ አነሳሱ። ቁርአን የትንሳኤ ቀን ለሚያነቡትና በርሱ ለሚተገብሩ ሰዎች ያማልዳል። ቀጥለውም የበቀራንና የአሉ ዒምራንን ምዕራፎች በማንበብ ላይ ጠንከር አድርገው አነሳሱ። ስለሚመሩና ስለሚያበሩም አብሪዎች ብለው ሰየሟቸው። እነርሱን የማንበብ፣ ትርጉማቸውን የማስተንተንና ውስጣቸው ባለው የመተግበር ምንዳና አጅርም የትንሳኤ ቀን እንደ ሁለት ደመና ወይም ሌላ ጥላ ወይም እርስ በርስ ተጠባብቀው ክንፋቸውን እንደዘረጉ ሁለት የበራሪ መንጋ ተመስለው ባለቤቶቻቸውን አስጠልለው የሚከላከሉለት መሆናቸውን ተናገሩ። አስከትለውም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የበቀራን ምዕራፍ አዘውትሮ በመቅራት፣ ትርጉሙን በማስተንተንና ውስጡ ባለው በመስራት ላይ አጠንክረው አነሳሱ። ይህም ውስጡ በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ትልቅ በረከትና ጥቅም ስላለው እና ይህንን መተውም የትንሳኤ ቀን ቁጭትና ፀፀት ይዞ ስለሚመጣ ነው። ከዚህ ምዕራፍ ደረጃዎች መካከልም ደጋሚዎች ይህንን ምዕራፍ የሚቀራን ሰው ሊጎዱ አለመቻላቸው ተጠቃሽ ነው።

فوائد الحديث

ቁርአንን አብዝቶ በመቅራት ላይ መታዘዙን፣ ቁርአን የትንሳኤ ቀን ለሚያነቡት፣ መመሪያውን ለሚይዙና ውስጡ በታዘዘው በመተግበር ለሚቆሙና ውስጡ የተከለከለውን ለሚተዉ ባለቤቶቹ እንደሚያማልድ እንረዳለን።

የበቀራንና የኣሊ ዒምራንን ምዕራፍ ያላቸውን ደረጃና ምንዳቸው የላቀ መሆኑን እንረዳለን።

የበቀራን ምዕራፍ መቅራት ያለውን ደረጃና ባለቤቱን ከድግምት እንደሚከላከል እንረዳለን።

التصنيفات

የምእራፎችና አንቀጾች ትሩፋቶች, የተከበረው ቁርአን ትሩፋቶች