إعدادات العرض
1- ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።
2- በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።
3- ከፍ ያለው አላህ እንዲህ አለ: 'ሶላትን በኔና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፈልኩት። ለባሪያዬም የጠየቀው አለው።
4- አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።
5- ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን