ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።

ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቶችን ከሶላት አራቁቶ እንደመቃብር የማይሰገድበት ማድረግን ከለከሉ። በመቀጠልም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ ከሚቀራበት ቤት እንደሚሸሽ ተናገሩ።

فوائد الحديث

ቤት ውስጥ ሱና ሶላቶችን የመሰሉ አምልኮዎችን ማብዛት እንደሚወደድ እንረዳለን።

ከጀናዛ ሶላት በስተቀር መቃብር ግቢ ውስጥ ሶላት መስገድ ወደ ሺርክና በተቀባሪው ላይ ወሰን ወደ ማለፍ ከሚያዳርሱ መንገዶች አንዱ ስለሆነ አይፈቀድም።

መቃብር ዘንድ መስገድ መከልከሉ ሶሐቦች ዘንድ የተረጋገጠ ጉዳይ ስለሆነ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቶችን ልክ እንደመቃብር የማይሰገድባቸው ከማድረግ ከለከሉ።

التصنيفات

የምእራፎችና አንቀጾች ትሩፋቶች