إعدادات العرض
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ…
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን
ከምእመናን እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው፦ "ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን ይቀሩበት ነበር። ከዚያም ከሰውነታቸው የቻሉትን በመዳፋቸው ያብሳሉ። (ሲያብሱም) ጭንቅላታቸውን፣ ፊታቸውንና ከሰውነታቸው የፊትለፊቱን በቅድሚያ ያብሳሉ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ይፈፅሙታል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Kurdî Moore Soomaali Français Wolof Oromoo Tagalog Українська Azərbaycan தமிழ் bm Deutsch ქართული Português Македонски Magyar Lingala Русский 中文الشرح
ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መመሪያ መካከል ለመተኛት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ ልክ ዱዐ እንደሚያረግ ሰው መዳፋቸውን ሰብስበው ከፍ ያደርጉት ነበር። በሱም ላይ ከትንሽ ምራቅ ጋር በመቀላቀል ቀለል ያለ መንፋት በአፋቸው እየነፉበት ሶስት ምእራፎች ያነቡበታል። {ሱረቱል ኢኽላስ}ን፣ {ሰረቱል ፈለቅ}ን፣ {ሱረቱ አንናስ}ን ከዚያም የቻሉትን ያህል የሰውነታቸውን ክፍል ከጭንቅላታቸው፣ ከፊታቸውና ከሰውነታቸው የፊትለፊት ክፍል በመጀመር በመዳፋቸው ያብሱታል። ይህንንም ድርጊት ሦስት ጊዜ ይደጋግሙታል።فوائد الحديث
ከመተኛት በፊት የኢኽላስን ምእራፍና ሙዐወዘተይንን መቅራትና ምራቅ የቀላቀለን ትንፋሽ በመንፋት የተቻለውን ያህል የሰውነትን ክፍል ማበስ እንደሚወደድ እንረዳለን።