አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።}…

አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።

ኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው- እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ውስጥ ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። " እርሳቸውም በድጋሚ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኡበይ ቢን ከዕብን የአላህ መጽሐፍ ውስጥ ትልቁ አንቀፅ ማን ናት? በማለት ጠየቁት። መልስ ለመስጠት ካመነታ በኋላ አየቱል ኩርሲይ ናት {አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} በማለት መለሰ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በዕውቀትና ጥበብ የተሞላ መሆኑን ለመጠቆም ደረቱን በመምታት በዚህ ዕውቀት እንዲደሰትና እንዲገራለት ዱዐ በማድረግ ትክክለኛ መልስ እንደመለሰ በመጥቀስ አበረታቱት።

فوائد الحديث

የኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው- ትልቅ ደረጃ፤

አየቱል ኩርሲይ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ትልቋ አንቀፅ በመሆኗ መሸምደዱ፣ ትርጉሙን ማስተንተኑና እርሱን መተግበር ተገቢ ነው።

التصنيفات

የምእራፎችና አንቀጾች ትሩፋቶች, የእውቀት ትሩፋት