إعدادات العرض
ከአንተ በፊት ማንም ያልተሰጠው በሆነ ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለት ብርሃኖች አበስርሃለሁ። (እነርሱም) የመጽሐፉ መክፈቻ (ፋቲሓ) እና የበቀራ ምዕራፍ መጨረሻዎቹ ናቸው። ከነርሱም…
ከአንተ በፊት ማንም ያልተሰጠው በሆነ ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለት ብርሃኖች አበስርሃለሁ። (እነርሱም) የመጽሐፉ መክፈቻ (ፋቲሓ) እና የበቀራ ምዕራፍ መጨረሻዎቹ ናቸው። ከነርሱም አንድም ፊደል አታነብም የሚሰጥህ ቢሆን እንጂ።
ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ጂብሪል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ተቀምጦ ሳለ ከበላዩ ድምፅ ሰማና ራሱን ቀና አደረገ። እንዲህም አለ: "ይህ ዛሬ የተከፈተ የሰማይ በር ነው። ከዛሬ በቀርም ተከፍቶ አያውቅም።" ከተከፈተው በርም መልአክ ወረደ። ጂብሪልም እንዲህ አለ: "ይህ ወደ ምድር የወረደ መልአክ ነው። ከዛሬ በቀርም በጭራሽ ወርዶ አያውቅም" መልአኩም ሰላምታን አቀረበና እንዲህ አለ: "ከአንተ በፊት ማንም ያልተሰጠው በሆነ ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለት ብርሃኖች አበስርሃለሁ። (እነርሱም) የመጽሐፉ መክፈቻ (ፋቲሓ) እና የበቀራ ምዕራፍ መጨረሻዎቹ ናቸው። ከነርሱም አንድም ፊደል አታነብም የሚሰጥህ ቢሆን እንጂ።"»
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Hausa Português मराठी دری বাংলা ភាសាខ្មែរالشرح
መልአኩ ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ተቀምጦ ሳለ ከሰማይ በር ሲከፈት እንደሚያሰማው አይነት ድምፅ ሰማ። ጂብሪልም ራሱንና አይኑን ወደ ሰማይ ቀና አደረገ። ቀጥሎ ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ይህ የሰማይ በር ዛሬ እንደተከፈተና ከዚህ ቀን በፊትም በፍፁም ተከፍቶ እንደማያውቅ ነገራቸው። ከሰማይም ወደ ምድር ከመልአኮች መካከል ከዛሬ በቀር ወርዶ የማያውቅ አንድ መልአክ ወረደ። መልአኩም ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሰላምታን አቀረበና እንዲህ አላቸው: ከአንተ በፊት ለማንም ነቢይ ባልተሰጡና ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለቱ ብርሃኖች አበስርሃለሁ። እነርሱም: የፋቲሓ ምዕራፍና የበቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዎቹ ሁለት አንቀጾች ናቸው። አስከትሎም መልአኩ እንዲህ አለ: አንድም ሰው ከነርሱ አንድ ፊደል እንኳ ብትሆን ካነበበ አላህ በውስጧ ያለውን መልካም ነገር፣ ተማፅኖና ፍላጎት ይሰጠዋል።فوائد الحديث
የፋቲሓ ምዕራፍና የበቀራ ምዕራፍ መጨረሻዎች ያላቸውን ደረጃና እነርሱን በመቅራትና ውስጣቸው ባለው መልዕክት በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ሰማይ መለኮታዊ ትእዛዛት የሚወርዱበት በሮች እንዳለውና የሰማይ በርም ያለ አላህ ትእዛዝ እንደማይከፈት እንረዳለን።
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጌታቸው ዘንድ ያላቸው ክብር ተገልጿል። ይኸውም ከርሳቸው በፊት ማንንም ነቢይ ባላከበረበት እርሳቸውን ማክበሩና እነዚህን ሁለት ብርሃኖች መስጠቱ ነው።
ወደ አላህ ከመጣሪያ መንገዶች መካከል በመልካም ማበሰር አንዱ ነው።