እኔ ሴቶችን አልጨብጥም። ለመቶ ሴቶች የምናገረው ቃል ለአንዲ ሴት እንደምናገረው ነው።

እኔ ሴቶችን አልጨብጥም። ለመቶ ሴቶች የምናገረው ቃል ለአንዲ ሴት እንደምናገረው ነው።

ከኡመይማህ ቢንት ሩቀይቃህ ረዺየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቃል ልንጋባ ከተወሰኑ የአንሷር ሴቶች ጋር ሆኜ መጣሁ። እንዲህም አልናቸው: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአላህ ላይ አንዳችንም ላናጋራ፤ ላንሰርቅ፤ ዝሙትን ላንሰራ፤ በእጆቻችንና በእግሮቻችን መካከል የምንቀጥፈውን ቅጥፈት ላንፈፅም፤ በመልካም ጉዳይም ላናምፅዎት ቃል እንጋባዎ" እርሳቸውም: "በቻላችሁት ጉዳዮችና አቅማችሁ በሚፈቅደው ጉዳዮች ቃል ተጋባኃችሁ!" አሉን። እኛም "አላህና መልክተኛው ለኛ የበለጠ አዛኝ ናቸው። የአላህ መልክተኛ ሆይ! ኑ እጅዎን ይዘርጉ ቃል እንጋባዎ።" አልን። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "እኔ ሴቶችን አልጨብጥም። ለመቶ ሴቶች የምናገረው ቃል ለአንዲ ሴት እንደምናገረው ነው። ወይም ልክ ለአንድ ሴት እንደምናገረው ነው።" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ኡመይማህ ቢንት ሩቀይቃህ ረdiየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተናገረችው እርሷ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ከተወሰኑ የአንሷር ሴቶች ጋር ሆና በአላህ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ፤ ላይሰርቁ፤ ዝሙት ላይሰሩ፤ በእጆችና በእግሮች መሃል የሚቀጥፉትን ላይፈፅሙ፤ በመልካም ነገር ላይ እርሳቸውን ላያምፁ ከርሳቸው ጋር ቃል ልትጋባ መጣች። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "በቻላችሁትና አቅማችሁ በሚፈቅዱ ጉዳዮች ላይ ቃል ተጋባኋቹህ።" እኛም: "አላህና መልክተኛው ለኛ የበለጠ አዛኝ ናቸው። የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከወንዶች ጋር ቃል ሲጋቡ እንደሚፈፅሙት ኑ እጅዎን ይዘርጉና በመጨባበጥ ቃል እንጋባዎ።" አልን። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "እኔ ሴቶችን አልጨብጥም። ለመቶ ሴቶች የምናገረውና ቃል የምጋባው ለአንድ ሴት እንደምጋባው ነው።"

فوائد الحديث

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሴቶችን ቃል የሚጋቡበት ሁኔታ መገለፁን እንረዳለን።

ከቅርብ ዘመድ ውጪ ያሉን ሴቶች መጨበጥ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

የሸሪዓ ትእዛዛትና ክልከላዎች አቅምና ችሎታ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን እንረዳለን።

التصنيفات

በወንድና በሴት መካከል የሚኖር ግንኙነት