ከዑክል ወይም ከዑረይና ጎሳ የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ መጡ። መዲና ስላልተስማማቸው ሆዳቸውን ታመሙ።

ከዑክል ወይም ከዑረይና ጎሳ የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ መጡ። መዲና ስላልተስማማቸው ሆዳቸውን ታመሙ።

ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከዑክል ወይም ከዑረይና ጎሳ የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ መጡ። መዲና ስላልተስማማቸው ሆዳቸውን ታመሙ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ወተት ወዳላቸው ግመሎች በመሄድ ከሽንታቸውና ከወተታቸው እንዲጠጡ አዘዟቸው። የተሻላቸውም ጊዜ የነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እረኛ ገድለው ግመሎቹን እየነዱ ሄዱ። የመግደላቸው ወሬም የቀኑ መጀመሪያ ላይ ደረሰ። ፈለጋቸውን አስተከትለውም ሰዎችን ላኩ። ቀኑ ረፈድ ያለ ጊዜም ተይዘው መጡ። በነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ትእዛዝ መሰረትም እጃቸውና እግራቸው ተቆረጠ። አይኖቻቸውም ተተኮሰ። ተኳሳ ድንጋይ ላይም ተጣሉ። ውሃን ይጠይቃሉ ግን ማንም አይሰጣቸውም ነበር። አቡ ቂላባ እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሰዎች ሰረቁ፤ ገደሉ፤ ከእምነት በኋላም ካዱ፤ አላህና መልክተኛውንም ተዋጉ።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ከዑክልና ዑረይና ጎሳ የሆኑ ሰዎች ሰልመው ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መጡ። ሆዳቸውን የነፋፋች በሽታ አመማቸው። የመዲናም ምግብና አየር ስላልተስማማቸው መዲና መቆየትን ጠሉ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለዘካ ወደ ተሰበሰበ ግመል ሄደው የግመል ሽንትና ወተት እንዲጠጡ አዘዟቸው። እነርሱም ወደዛ ሄዱ። ጤነኞች የሆኑ፣ የወፈሩና መልካቸውም የተመለሰ ጊዜ የነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እረኛ ገለው ግመሉን እየነዱ ሄዱ። ወሬውም የቀኑ መጀመሪያ ላይ ተሰማ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እነርሱን ለመፈለግ ሰዎች ላኩ። የተላኩትም ሰዎች አገኟቸው። ረፋድ የሆነ ጊዜ ተማርከው ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መጡ። እረኛው ላይ በፈፀሙት መልኩ እጆቻቸውና እግሮቻቸው እንዲቆረጥ፤ አይኖቻቸው እንዲጠፋ አዘዙ። ሀሩራማ ድንጋይ ላይም ተጣሉ። እስኪሞቱ ድረስም ውሃ እንዲያጠጧቸው ሰውን ቢማፀኑም ማንም አላጠጣቸውም። አቡ ቂላባም እንዲህ አለ: "እነዚህ ሰዎች ሰረቁ፤ ገደሉ፤ ከእምነት በኋላም ካዱ፤ አላህና መልክተኛውንም ተዋጉ።"

فوائد الحديث

ስጋው የሚበላ እንስሳ ሽንቱ ንፁህ እንደሆነ እንረዳለን።

በግመል ሽንትና ወተት መታከምና እንደመዳኒትነት መገልገል የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።

በቂሷስ (የገደለን በመግደል ቅጣት) ወቅት ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ቅጣቱን መፈፀም በሸሪዓ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን። አካልን ቆራርጦ መግደል የሚከለክለው ሐዲሥም ከቂሷስ ውጪ ባሉ ጊዜያት ነው በሚል ይተረጎማል።

በሽፍትነትም ይሁን አዘናግተው አንድን ሰው የገደሉ በርካታ ሰዎች በአንድ ሰው ግድያ ሁሉም እንደሚገደሉ እንረዳለን።

التصنيفات

ነቢያዊ ህክምና, የሽፍታዎች መቅጫ ህግ, ከኢስላም የወጡ ሰዎች መቅጫ ህግ