إعدادات العرض
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) ለመስገድ የሚያደርጉትን አይነት መጠባበቅ ለሌላ ሱና ሶላት አድርገው አይጠባበቁም ነበር።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) ለመስገድ የሚያደርጉትን አይነት መጠባበቅ ለሌላ ሱና ሶላት አድርገው አይጠባበቁም ነበር።
ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) ለመስገድ የሚያደርጉትን አይነት መጠባበቅ ለሌላ ሱና ሶላት አድርገው አይጠባበቁም ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንዲህ ብላ ተናገረች: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) እጅግ ተጠባብቀውና ዘውትረው እንደሚሰግዱት ያህል ምንም ሱና ሶላት ተጠባብቀውና ዘውትረው አይሰግዱም ነበር።فوائد الحديث
ነዋፊል (ተጨማሪ) ሶላቶች የሚባሉት: ከግዴታ ሶላቶች ውጪ ያሉ ማለት ነው። እዚህ ሐዲሥ ላይ የተፈለገውም ከግዴታ ሶላቶች በፊትና በኋላ ተከትለው የሚሰገዱ ሶላቶች ማለት ነው።
ሱነን አርረዋቲብ የሚባሉት: ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ፣ ከዝሁር በፊት አራት ረከዓ ከዝሁር በኋላ ሁለት ረከዓ፣ ከመግሪብ በኋላ ሁለት ረከዓ፣ ከዒሻ በኋላ ሁለት ረከዓ ናቸው።
የፈጅር ቀብሊያ በመኖርያ ሀገር ላይም ሆነ ጉዞ ላይ ይሰገዳል። የዝሁር፣ የመግሪብና የዒሻ ቀብሊያና ባዕዲያ ሶላቶች ግን በመኖርያ ሀገር ላይ ብቻ ነው የሚሰገዱት።
የፈጅር ሁለቱ ረከዓ ቀብሊያ አፅንዖት የተሰጠው ተወዳጅ ሶላት ስለሆነ ችላ ሊባል አይገባውም።