إعدادات العرض
1- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከዝሁር በፊት አራት ረከዓና ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ አይተዉም ነበር።
2- ከዝሁር በፊት አራት ረከዓዎች ላይና ከዝሁር በኋላ አራት ረከዓዎች ላይ የተጠባበቀ ሰው አላህ እሳትን በርሱ ላይ እርም አድርጎለታል።
3- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) ለመስገድ የሚያደርጉትን አይነት መጠባበቅ ለሌላ ሱና ሶላት አድርገው አይጠባበቁም ነበር።