إعدادات العرض
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከዝሁር በፊት አራት ረከዓና ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ አይተዉም ነበር።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከዝሁር በፊት አራት ረከዓና ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ አይተዉም ነበር።
የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦ "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከዝሁር በፊት አራት ረከዓና ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ አይተዉም ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو हिन्दी Français 中文 Kurdî Português Русский Nederlands Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી Kiswahili پښتو සිංහල Hausa ไทย മലയാളം नेपालीالشرح
እናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እርሷ ቤት ውስጥ በሱና ሶላቶች ይዘወትሩ እንደነበር ተናገረች። እነዚያ ሱና ሶላቶችም ከዝሁር ሶላት በፊት በሁለት ማሰላመት አራት ረከዓ ሶላትና ከፈጅር ሶላት በፊት ደግሞ ሁለት ረከዓ ሶላት ናቸው።فوائد الحديث
ከዝሁር ሶላት በፊት አራት ረከዓ ሶላት ላይና ከፈጅር ሶላት በፊት ደግሞ ሁለት ረከዓ ሶላት ላይ መጠባበቅ እንደሚወደድ እንረዳለን።
በላጩ ሱና ሶላቶች ቤት ውስጥ መሰገዳቸው ነው። ስለዚህ ጉዳይ የተናገረችው ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ‐ መሆኗም ከዛ አንፃር ነው።
التصنيفات
ከግዴታ ሶላት በፊትና በኋላ የሚሰገዱ ሱና ሶላቶች