إعدادات العرض
አቡ በክር ሆይ! አላህ ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉ።
አቡ በክር ሆይ! አላህ ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉ።
ከአቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እኛ ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን የአጋርያን እግር ከጭንቅላታችን በላይ ሆኖ ተመለከትኩት። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ: ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመለከተን ነበር።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Русский Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
የአማኞች መሪ አቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በስደት ወቅት ስለነበረው ሁኔታ ሲተርኩ እንዲህ አሉ: እኛ የሠውር ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን ከጭንቅላታችን በላይ የአጋርያን እግር ሆኖ ተመለከትኩ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመከተናል።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ በእርዳታው፣ በእገዛውና በጥበቃው ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉት።فوائد الحديث
አቡበክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመካ ወደ መዲና በሚሰደዱበት ወቅት ቤተሰብና ገንዘባቸውን ትተው መጎዳኘታቸው የነበራቸውን ማዕረግ ያሳየናል።
አቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በወቅቱ የነበራቸውን ስጋት፣ ለአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የነበራቸውን ጥልቅ ውዴታና ጠላቶች እርሳቸውን እንዳያጠቁ የነበራቸውን ስጋት እንመለከታለን።
በአላህ ላይ መተማመንና ጥንቃቄን በመያዝ ጥረት ካደረጉ በኋላ በርሱ ጥበቃና እንክብካቤ መረጋጋት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
አላህ ለነቢያቶቹና ለወዳጆቹ ትኩረት መስጠቱንና ለነርሱም በእርዳታው እንደሚንከባከባቸው እንረዳለን። አላህ እንዲህ ብሏል: {እኛ መልክተኞቻችንን፣ እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ህይወት ምስክሮችም በሚቆሙበት ቀን በእርግጥ እንረዳለን።}
ይህ ሐዲሥ በአላህ ላይ የተመካ ሰው አላህ እንደሚበቃው፣ እንደሚረዳው፣ እንደሚያግዘውና እንደሚጠብቀው ያስገነዝበናል።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በጌታቸው ላይ ያላቸው የተሟላ መመካትን እንረዳለን። እርሳቸው በአላህ ላይ የሚመኩና ጉዳያቸውን ሁሉ ወደርሱ የሚያስጠጉ ነበሩ።
የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጀግንነትና ቀልብና ነፍስን ያረጋጉ እንደነበር እንረዳለን።
ጠላትን በመፍራት ሃያማኖትን አስጠብቆ መሸሽና ሰበብንም ማድረስ እንደሚገባ እንረዳለን።