إعدادات العرض
ሰዎች የትንሳኤ ቀን ባዶ እግራቸውን፣ ራቁትና ያልተገረዙ ሆነው ይሰበሰባሉ።
ሰዎች የትንሳኤ ቀን ባዶ እግራቸውን፣ ራቁትና ያልተገረዙ ሆነው ይሰበሰባሉ።
ከአማኞች እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: «የአላህ መልክተኛን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ "ሰዎች የትንሳኤ ቀን ባዶ እግራቸውን፣ ራቁትና ያልተገረዙ ሆነው ይሰበሰባሉ።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ወንዶችም ሴቶችም ባጠቃላይ ከፊሉ ወደ ከፊሉ እየተመለከተ?" አልኳቸው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ዓኢሻህ ሆይ! ጉዳዩኮ ከፊሉ ወደ ከፊሉ ከመመልከትም በላይ በጣም ከባድ ነው።" አሉኝ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የትንሳኤ ቀን የሚከሰተውን አንድ ክስተት እንዲህ በማለት ገለፁ። ሰዎች ለሒሳብ ከቀብራቸው ከተቀሰቀሱ በኋላ ያለ ጫማ በባዶ እግራቸው፣ ያለልብስ ሰውነታቸው ተራቁቶና እናታቸው እንደወለደቻቸው ቀን ያልተገረዙ ሆነው ይሰበሰባሉ። ይህንንም የአማኞች እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ስትሰማ ተደንቃ እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ወንዶችም ሴቶችም ባጠቃላይ ከፊሉ ወደ ከፊሉ እየተመለከተ?" ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከሞት መቀስቀስ በኋላ የመሰብሰብና የመቆም ጉዳይ ሀፍረተ ገላን ከመመልከትም በላይ የሰዎችን ሃሳብና አይን የሚሰልብ አስደንጋጭነት እንዳለው ገለፁ።فوائد الحديث
የትንሳኤ ቀን አስደንጋጭነት መገለፁ። የሰው ልጅ የዛን ቀን ስለ ሒሳቡና ስራዎቹ ከማሰብ ውጪ አንዳችም ነገር አያጠምደውም።
ይህ ሐዲሥ የሰው ልጅ ካልተዘናጋ በቀር ወንጀል ላይ እንደማይወድቅ ያጠናክርልናል። የሰው ልጅ ያመፀውን ጌታ ታላቅነት ወይም የቅጣቱን ከባድነት ቢያስታውስ ኖሮ ለቅፅበት ያህል እንኳ እርሱን ከማውሳት፣ ከማመስገንና አሳምሮ ከማምለክ አይዘናጋም ነበር። ስለዚህም ነው የትንሳኤ ቀን የሚሰበሰቡ ሰዎች በነፍሳቸው ከመጠመዳቸው የተነሳ ከፊሉ ወደ ከፊሉ የማይመለከት ሆኖ ታየዋለህ።
በአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘመን የነበሩ ሴቶች የነበራቸው ሃፍረት ከፍተኛ እንደሆነ እንረዳለን። ይኸውም ዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ወንዱም ይሁን ሴቱ ፍጥረታት ባጠቃላይ ራቁታቸውን እንደሚቀሰቀሱ ስትሰማ ሃፍረት በተሞላበት መልኩ ማብራሪያ ከመጠየቋ የምንረዳው ነው።
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "ሁሉም ስለራሱ ጉዳይ የተጠመደ በመሆኑ ስለ ወንድሙ ሁኔታ ምንም አያውቅም። ታላቁ አላህ እንዲህ ብሏል: {ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ሁኔታ አለው።} [ዐበሰ: 37] አንድም ሰው ወደ ሌላው ሃፍረተ ገላ ሊመለከት እንኳ አይዞርም።"
ግርዛት: ለወንድ ልጅ: ክርክሩን የሸፈነውን ቆዳ መቁረጥ ሲሆን ለሴት ደግሞ: ከብልት መግቢያ ቀዳዳ ከፍ ብሎ ያለውን የአውራ ዶሮ ቆብ የሚመስለውን ቆዳ መቁረጥ ነው።
التصنيفات
የመጨረሻው ህይወት