إعدادات العرض
ሁሉም የሰው ልጅ መገጣጠሚያ አጥንቶች ምፅዋት አለባቸው።
ሁሉም የሰው ልጅ መገጣጠሚያ አጥንቶች ምፅዋት አለባቸው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሁሉም የሰው ልጅ መገጣጠሚያ አጥንቶች ምፅዋት አለባቸው። ፀሐይ በምትወጣበት ቀናት ሁሉ በሁለት ሰዎች መካከል ማስታረቅ ምፅዋት ነው፤ ሰውዬውን መጓጓዣው ላይ እንዲወጣ ማገዝ፣ እርሷ ላይ ማሸከም ወይም እቃውን እርሷ ላይ መጫን ምፅዋት ነው፤ መልካም ንግግር ምፅዋት ነው፤ ወደ ሶላት የምትራመዳት ሁሉም እርምጃ ምፅዋት ነው፤ ከመንገድ ላይ ቆሻሻን ማስወገድ ምፅዋት ነው።"
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் ไทย Deutsch پښتو অসমীয়া Shqip Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Română Magyar Čeština Moore Malagasy Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayuالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁሉም ቀን በሁሉም ለአቅመ አዳም በደረሰ ሙስሊም ላይ ሁሉ በመገጣጠሚያ አጥንቶቹ ቁጥር ያህል አላህ ለሰጠው ጤንነት ለማመስገንና አጥንቶቹን መጨበጥና መዘርጋት በሚችል መልኩ ስለገጣጠመው ለአላህ ብሎ መመፅወት እንደሚገባው ገለፁ። ይህቺም ምፅዋት በመልካም ተግባራት ባጠቃላይ እንደሚፈፀምና ገንዘብ በመስጠት ላይ ብቻ እንዳልታጠረ ገለፁ። ከነርሱም መካከል: በተጣሉ ሁለት ሰዎች መካከል ማስታረቅና መፍረድ ምፅዋት ነው። መጓጓዣው ላይ ለመውጣት ለተሳነው ሰውዬ በማሰቀልህ ወይም እቃውን በመጫን ማገዝህ ምፅዋት ነው። ዚክር፣ ዱዓ ማድረግ፣ ሰላምታ ማቅረብና ሌሎችም መልካም ንግግሮች ምፅዋት ናቸው። ወደ ሶላት የምትራመዳት ሁሉም እርምጃ ምፅዋት ናት። መንገድ ላይ የሚያውክን ነገር ማስወገድም ምፅዋት ነው።فوائد الحديث
የሰው ልጅ አጥንቶች ተገጣጥመው መሰራታቸውና የነርሱም ደህና መሆን ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎች መካከል እንደሆነ እንረዳለን። ለያንዳንዱ ፀጋ የሚያቀርበው ምስጋና እንዲሞላም ለሁሉም አጥንት መመፅወት አስፈላጊ ነው።
ይህ የአላህ ፀጋ እንዲዘወትርም ምስጋናን በየቀኑ በማደስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
በየቀኑ ግዴታ ያልሆኑ ስራዎችን በመስራትና ምፅዋት በማድረግ ላይ በመዘውተር መነሳሳቱን እንረዳለን።
በሰዎች መካከል ማስታረቅ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
ወንድምን በማገዝ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህም ወንድምን ማገዝ ምፅዋት ስለሆነ ነው።
የጀመዓ ሶላት በመገኘት ላይ፣ ወደርሱ በመሄድ ላይና መስጂድ በመገኘት መስጂድን በማሳመር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ሙስሊሞች የሚያውካቸውንና የሚጎዳቸውን ነገር በማራቅ የሙስሊሞችን መንገድ ማስከበር ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።
