إعدادات العرض
ይህቺ ለልጇ ካላት እዝነት የበለጠ አላህ ለባሮቹ ያዝንላቸዋል።" አሉ።
ይህቺ ለልጇ ካላት እዝነት የበለጠ አላህ ለባሮቹ ያዝንላቸዋል።" አሉ።
ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ምርኮኞች ገቡ። ድንገት ከምርኮኞቹ መካከል አንድ ሴት ጡቶቿን እያለበች ልጅን የምታጠባ ነበረች። ከምርኮኞች መካከል ልጇን ስታገኝ ያዘችውና ወደ ሆዷ አስጠግታ ጡቷን አጠባችው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለኛ እንዲህ አሉን: "ይህቺ ሴትዮ ልጇን እሳት ውስጥ ትጥላለች ብላችሁ ታስባላችሁን?" እኛም "አለመጣል እስከቻለች ድረስ በፍፁም አትጥለውም።" አልን። እርሳቸውም "ይህቺ ለልጇ ካላት እዝነት የበለጠ አላህ ለባሮቹ ያዝንላቸዋል።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî Magyar ქართული Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የሃዋዚን ምርኮኞች መጡላቸው። ድንገት ከነርሱ መካከል አንዲት ሴት ልጇን ትፈልግ ጀመር። አንድ ህፃን ስታገኝም ወተት በጡቷ ውስጥ በመጠራቀሙ ስለተጎዳች ትይዘውና ታጠባዋለች። ከምርኮኞች መካከልም ልጇን አግኝታ ያዘችውና ወደ ሆዷ አቅፋ ደግፋ አጠባችው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለባልደረቦቻቸው እንዲህ አሉ: "ይህቺ ሴትዮ ልጇን እሳት ውስጥ ትጥላለች ብላችሁ ታስባላችሁን?" እኛም "በራሷ ፍቃድ ማንም ሳያስገድዳት መቼም አትጥለውም።" አልናቸው። እርሳቸውም "አላህ ለሙስሊም ባሮቹ ይህቺ ለልጇ ካላት እዝነት የበለጠ እጅግ አዛኝ ነው።" አሉ።فوائد الحديث
አላህ ለባሮቹ ያለውን ሰፊ እዝነት እንረዳለን። አላህ ለባሮቹ መልካምን፣ ጀነትንና ከእሳት መዳንን ይፈልግላቸዋል።
ድንገት ከሚከሰቱ ክስተቶች ትምህርትን መውሰድና ከማስተማርና ምክር ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ እንረዳለን።
አማኝ የሆነ ሰው በአላህ ላይ ጥሩ እሳቤ ሊኖረው ይገባል። አላህን ከመፍራትና በዲኑ ላይ ከመፅናቱ ጋር ተስፋ መቁረጥ የለበትም። ጥራት የተገባው አላህ የሰፊ እዝነት ባለቤት ነውና።
التصنيفات
አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል