እነዚህ (የቤት) እንስሶች እንደ ዱር እንስሶች የዱር ባህሪ አላቸው። ከነርሱ መካከል አልያዝ ብሎ ያሸነፋችሁ ላይ እንደዚሁ አድርጉ።

እነዚህ (የቤት) እንስሶች እንደ ዱር እንስሶች የዱር ባህሪ አላቸው። ከነርሱ መካከል አልያዝ ብሎ ያሸነፋችሁ ላይ እንደዚሁ አድርጉ።

ከራፊዕ ቢን ኸዲጅ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «በዙል ሑለይፋ ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጋር ነበርን። ሰዎች ለረሃብ ተጋለጡ። ግመሎችና ፍየሎች በምርኮ አግኝተው ነበር።» ራፊዕ እንዲህ አለ: «ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰዎች ኋላ ነበሩ። (እርሳቸውን ከመጠበቅ) ቸኮሉና አረዱ። ድስጥ ላይም ጣዱ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሲደርሱ ድስጡ እንዲደፋ አዘዙና ተደፋ። ከዚያም ምርኮውን አከፋፈሉ። የአስር ፍየልን ዋጋ በአንድ ግመል እያደረጉ አከፋፈሉ። አንድ ግመል ግን ፈረጠጠ። እርሱን ሲፈልጉም አደከማቸው። በመካከላቸው የነበረው የፈረስ ቁጥርም ትንሽ ነበር። ከመካከላቸው አንድ ሰውዬ በቀስቱ ወጋውና አላህ አቆመላቸው። ቀጥለው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "እነዚህ (የቤት) እንስሶች እንደ ዱር እንስሶች የዱር ባህሪ አላቸው። ከነርሱ መካከል አልያዝ ብሎ ያሸነፋችሁ ላይ እንደዚሁ አድርጉ።"» ራፊዕ እንዲህ ብሎም ጠየቃቸው: «እኛ ነገ ከጠላት ጋር እንገናኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን ወይም እንሰጋለን። የምናርድበት ቢላም የለንም። በተሳለ ቀርከሃ እንረድን? እርሳቸውም: "ከጥርስና ከጥፍር ውጪ ደምን ያፈሰሰና ሲታረድ የአላህ ስም የተወሳበትን ብሉ። የዚህንም ምክንያት እነግራችኋለሁ። ጥርስ የማታርዱበት አጥንት ስለሆነ ነው፤ ጥፍር የማታርዱበት ደግሞ የሐበሾች ስለት ስለሆነ ነው።" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ራፊዕ ቢን ኸዲጅ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዙል ሑለይፋ ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጋር እንደነበር ተናገረ። ሰዎችንም ረሃብ አጋጠማቸው። ከአጋርያን የማረኩት ፍየሎችና ግመሎች ነበሩ። ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሳያስፈቅዱም ምርኮ ከመከፋፈሉ በፊት ቸኮሉና አረዱ። ድስጥ ላይም ጣዱት። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰዎች ኋላ ነበሩ። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ያደረጉትን ሲያውቁ ድስጧ እንድትደፋ አዘው ከነመረቁ አስደፉት። ቀጥለው ምርኮዉን አከፋፈሉ። አስር ፍየሎችን በአንድ ግመል ተለዋጭ እያደረጉ አከፋፈሉ። ከነዚህ ግመሎችም አንድ ግመል ሸሸ። የነበራቸው ፈረስ ትንሽ ነበረና እርሱ ላይ መድረስ አቃታቸው። ከመካከላቸው የነበረ አንድ ሰውዬም በቀስት ወጋው። አላህም አቆመላቸው። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "እነዚህ ለማዳ እንስሶችም የዱር ባህሪ አላቸው። ከነርሱ መካከል ለመያዝ ያቃታችሁና ያሸነፋችሁን እንደዚሁ አድርጉት።" ራፊዕም እንዲህ አለ: "እኛ ነገ ጠላትን እንገናኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በመሳሪያዎቻችን እንዳናርድ ስለቱን እንዳይጎዳብን ያሰጋናል። ማረዳችን ደግሞ ግድ ነው። እኛ ጋር ደግሞ ቢላ የለንምና በደረቀ ስለታማ ቀርከሃ እንረድን?" ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ከጥርስና ከጥፍር ውጪ ደምን አብዝቶ ያፈሰሰና ሲታረድ የአላህ ስም የተወሳበትን ብሉ። የሁለቱንም ምክንያት እነግራችኋለሁ። ጥርስ የማታርዱበት አጥንት ስለሆነ ነው። ጥፍር የማታርዱበት ደግሞ የሐበሻ ከሃዲዎች ለማረድ የሚጠቀሙበት ስለሆነ ነው።" አሉ።

فوائد الحديث

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰራዊት ኋላ መጓዛቸው፣ ባልደረቦቻቸውን መጠባበቃቸውና መከታተላቸው፣ የባልደረቦቻቸውን ረዲየሏሁ ዐንሁም ምክር መቀበላቸው የርሳቸውን ትህትና በግልፅ ያስረዳናል።

መሪ የሆነ ሰው ህዝቦቹንና ሰራዊቱን ስርዓት ማስያዝ አለበት። የርሳቸውን ፈቃድ ከማግኘታቸው በፊት መጣደፋቸውንና ይህ ሁኔታቸውን ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ፍላጎታቸውን በመከልከል ስርዓትን አስተማሩበት።

ሶሐቦች ረዲየሏሁ ዓንሁም የነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ትእዛዛት በፍጥነት እንደሚቀበሉ እንረዳለን።

ምርኮ ከመከፋፈሉ በፊት መውሰድ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

ፍትሃዊነትን መላበስ ‐ በተለይ ጠላቶችንና ከሃዲያንን በምንታገልበት ስፍራ ‐ የድልና ጠላቶችን የማሸነፊያ አንዱ ሰበብ ነው።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "የቤት እንስሳ የዱር ባህሪ ካሳየ ግመል ወይም ከብት ወይም ፈረስ ወይም ፍየልና የመሳሰሉት መፈርጠጣቸውን ይመስል ብይናቸው እንደ ታዳኝ እንስሳ ነው። በቀስት ውርወራ መግደል ይፈቀዳል።"

እንስሳ መመገቡ ሐላል እንዲሆን ማረዱ ግዴታ ነው። እንስሳን ለመብላት እነዚህ ነገሮች መሟላታቸው መስፈርት ነው: 1 - መብላቱ የተፈቀደ እንስሳ መሆን አለበት። 2 - መይያዝ የሚችል እንስሳ መሆን አለበት። መይያዝ የማይቻል ከሆነ ግን የርሱ ብይን የአደን ብይን ነውና ማረድ መስፈርት አይደለም። 3 - የየብስ እንስሳ መሆን አለበት። የባሕር እንስሳ ከሆነ ማረዱ መስፈርት አይደለም።

የትክክለኛ እርድ መስፈርቶች: 1 - አራጁ ለእርድ ብቁ መሆን አለበት። አይምሮው ጤነኛ፣ (ጥሩውን ከመጥፎው) የለየ፣ ሙስሊም ወይም የመጽሐፍ ባለቤት መሆን አለበት። 2 - እርዱን ሲጀምር የአላህን ስም ማውሳት አለበት። 3 - የእርድ መሳሪያው ለእርድ ብቁ መሆን አለበት። ከጥርስና ከጥፍር ውጪ የተሰራ ሆኖ ስለታም መሳሪያ መሆን አለበት። 4 - ተይዞ መታረድ የሚችል እንስሳ ከሆነ እርዱ የጉሮሮውን ልዩ ደም ስሮችን በመበጠስ የእርድ ቦታው ላይ መሆን አለበት።

التصنيفات

አስተራረድ