የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ባጠቃላይ ይበልጥ ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ ሰው ነበሩ።

የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ባጠቃላይ ይበልጥ ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ ሰው ነበሩ።

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ባጠቃላይ ይበልጥ ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ ሰው ነበሩ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ሁሉ ስነምግባራቸው እጅግ የተሟላ ሰው ናቸው። ንግግርን በማሳመር፣ መልካምን በመለገስ፣ ፊታቸው በመፍታት፣ መጥፎ ከመስራት በመቆጠብ፣ ሌሎች የሚያደርሱባቸውን ጉዳት በመቻል በሁሉም ስነምግባሮችና መልካምነት ባጠቃላይ ግንባር ቀደም ናቸው።

فوائد الحديث

የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ምሉዕ መሆኑን እንረዳለን።

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመልካም ስነምግባር የተሟሉ ተምሳሌት ናቸው።

በመልካም ስነምግባር ዙሪያ ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መከተል መነሳሳቱን እንረዳለን።

التصنيفات

ስነ-ምግባሪያዊ ባህሪያቸው