إعدادات العرض
የሚያሳልፉት ቤተሰባቸውን በማገልገል ነው። ሶላት ሲደርስ ሶላት ለመስገድ ይወጣሉ።" አለች።
የሚያሳልፉት ቤተሰባቸውን በማገልገል ነው። ሶላት ሲደርስ ሶላት ለመስገድ ይወጣሉ።" አለች።
ከአስወድ ቢን የዚድ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ዓኢሻን ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቤት ውስጥ ስለሚሰሩት ስራ ጠየቅኳት? እርሷም: "የሚያሳልፉት ቤተሰባቸውን በማገልገል ነው። ሶላት ሲደርስ ሶላት ለመስገድ ይወጣሉ።" አለች።»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල ئۇيغۇرچە Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili मराठी Română অসমীয়া ไทย Hausa Português دری ភាសាខ្មែរالشرح
የአማኞች እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቤታቸው ውስጥ ስለነበራቸው ሁኔታ ተጠየቁ። ጊዜያቸውን እንዴት ነበር ያሳልፉ ይሰሩ የነበሩት? እርሷም: እንደማንኛውም ሰው እርሳቸውም ሰው ነበሩ። ወንዶች ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩትን ይሰሩ ነበር። ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ያገለግሉ ነበር። ፍየላቸውን ያልባሉ፣ ልብሳቸውን ይሰፋሉ፣ ጫማቸውን ይጠግናሉ፣ የተቀደደ ባልዲያቸውን ይለጥፋሉ። ሶላት ኢቃም የሚልበት ወቅት ላይ ሲደርሱ ምንም ሳያዘገዩ ወደርሷ ይወጣሉ በማለት መለሰች።فوائد الحديث
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የነበራቸውን የተሟላ መተናነስና ለቤተሰባቸው የነበራቸውን በጎነት እንረዳለን።
ዱንያዊ ስራዎች ባሪያዎችን ከሶላት ሊያዘናጓቸው እንደማይገባ እንረዳለን።
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሶላትን በመጀመሪያ ወቅት ላይ በመስገድ እንደዘወተሩ እንረዳለን።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ በመተናነስ ላይ፣ ኩራትን በመተውና ሰውዬው ቤተሰቡን እንዲያገለግል መነሳሳቱን እንረዳለን።"