إعدادات العرض
ሰዎች ጁመዓዎችን ከመተው ይከልከሉ! አለበለዚያ ግን አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽጋል። ከዚያም ከዝንጉዎች ይሆናሉ።
ሰዎች ጁመዓዎችን ከመተው ይከልከሉ! አለበለዚያ ግን አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽጋል። ከዚያም ከዝንጉዎች ይሆናሉ።
ከዐብደላህ ቢን ዑመርና አቡ ሁረይራ ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እነርሱ የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሚንበራቸው እንጨት ላይ ሆነው እንዲህ ሲሉ ሰሙ: "ሰዎች ጁመዓዎችን ከመተው ይከልከሉ! አለበለዚያ ግን አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽጋል። ከዚያም ከዝንጉዎች ይሆናሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Tiếng Việt Bahasa Indonesia Nederlands Kiswahili অসমীয়া English ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دری বাংলা Kurdîالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሚንበራቸው ላይ ሆነው ጁመዓን ያለምንም ተቀባይ ምክንያት በስንፍናና በማቃለል ከመተውና ከርሱ ወደኃላ ማለትን አስጠነቀቁ። ያለበለዚያ ግን አላህ በልቦቻቸው ላይ እንደሚያሽግና እንደሚሸፍን፤ በቀልባቸው ላይ እውነትን ከመከተል የሚያቅብ ግርዶሽ እንደሚያደርግና ከዚያም ከመልካም መንገዶች ከሚዘናጉትና ነፍሳቸውም ከአምልኮ ቸልተኛ ከሆኑት እንደምትሆን ተናገሩ።فوائد الحديث
ከጁመዓ ሶላት በመቅረት ጉዳይ ጠንካራ ዛቻ መምጣቱንና ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ መሆኑን እንረዳለን።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የጁሙዓ ሶላት የነፍስ ወከፍ ግዴታ መሆኑን ያስረዳናል።"
ለኹጥባ ሚንበርን ማዘጋጀት የተደነገገ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "የሐዲሡ ሀሳብ ከሁለት አንዱ የግድ የሚከሰቱ ናቸው ማለት ነው። ወይ ጁመዓዎችን ከመተው መቆጠብ ወይም አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽጋል። ጁመዓ መተውን መልመድ ቀልብ እንድትሸፈን ይገፋታል። ነፍስንም ከአምልኮ ቸልተኛ ያደርጋታል።"
መካሪና ገሳጭ የሆነ ሰው ሊመክራቸው ያሰባቸውን ግለሰቦች ደበቅ ሊያደርግም ይገባል። ይህም ምክሩ ተቀባይነት እንዲያገኝና ትእዛዙ ተፈፃሚ እንዲሆን የሚያደርግ ስለሆነ ነው።
التصنيفات
Virtue of Friday