አማኝ የሆነ ሰው ክልክል የሆነን ደም እስካላፈሰሰ ድረስ በሃይማኖቱ ነፃነት ውስጥ ከመሆን አይወገድም።

አማኝ የሆነ ሰው ክልክል የሆነን ደም እስካላፈሰሰ ድረስ በሃይማኖቱ ነፃነት ውስጥ ከመሆን አይወገድም።

ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዓንሁማ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል "አማኝ የሆነ ሰው ክልክል የሆነን ደም እስካላፈሰሰ ድረስ በሃይማኖቱ ነፃነት ውስጥ ከመሆን አይወገድም።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አማኝ የሆነ ሰው በመልካም ስራዎቹ ላይ ነፃነትና የአላህ እዝነት፣ ምህረትና ይቅርታው ውስጥ ከመሆን እንደማይወገድ ተናገሩ። መግደሉ ክልክል የሆነን ሰው የገደለ ጊዜ ግን ስራው የግድያውን ወንጀልና ይህን ትልቅ ወንጀሉን ስለማትሸፍን ስራው ትጠብበታለች።

فوائد الحديث

ያለአግባብና ሆን ብሎ የመግደልን ከባድነት እንረዳለን። ይህም አማኝን በሃይማኖቱ ከነበረው ነፃነት ወደ መጣበብ ያወጣዋልና።

ክልክል የሆኑ ደሞች አራት አይነቶች ናቸው። 1 - የሙስሊም ደም። ይህም እጅግ ከባዱ ነው። 2 - የዚሚይ ደም። ዚሚይ ማለት በሃይማኖታቸው ፀንተው በሙስሊም ሃገር ውስጥ እየኖሩ ለሙስሊሞች ግብር በመክፈልና የሙስሊሞችን ህግና ደንብ በማክበር የሚኖሩ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ናቸው። 3 - የሙዓሃድ ደም። እነርሱም በነርሱና በኛ መካከል ላንወጋቸውና ላይወጉን የጦር ቃልኪዳን የተስማማናቸው በሀገራቸው የሚኖሩ ከሃዲዎች ናቸው። 4 - የሙስተእሚን ደም ነው። እርሱም በኛና በርሱ መካከል ቃልኪዳንም ሆነ የግብር መክፈል ውል የሌለ ሙስሊሞችን የሚዋጋ ከሃዲ ሲሆን ነገር ግን ለተወሰነ ወቅት ከመሪው ወይም ለዚህ ከተሾመ የሚመለከተው አካል ወደ ሙስሊሞች ሃገር እንዲገባ ደህንነት የተሰጠው ሰው ነው።

التصنيفات

ማቁሰል