إعدادات العرض
ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።
ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።
ከአቡ ሩቀየህ ተሚም ቢን አውስ አድዳሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ፦ "ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።" እኛም "ለማን ነው (የምንቆረቆረው) ታማኝ የምንሆነው?" አልናቸው። እሳቸውም "ለአላህ፣ ለመጽሐፉ፣ ለመልክተኛው፣ ለሙስሊሞች መሪዎችና ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ።" አሉ።
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch پښتو অসমীয়া Shqip Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Yorùbá Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Română Magyar Čeština Moore Malagasy Fulfulde Italiano Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ Bambara ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayu Yaoالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዲን የቆመው ስራን አላህ ግዴታ ባደረገው መልኩ ያለምንም ማጓደል ወይም ያለምንም ማታለል በመፈፀም ስራን ለአላህ በማጥራት (በኢኽላስ) እና በእውነተኝነት ላይ በመመርኮዝ መሆኑን ተናገሩ። ለነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ታማኝ (ተቋርቋሪ) የምንሆነው ለማን ነው?" ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም: የመጀመሪያው: ለአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስራን ለርሱ በማጥራት፣ በርሱ ባለማጋራት፣ በጌትነቱ በተመላኪነቱና በስሞቹና በባህሪያቶቹ በማመን፣ ትእዛዙን በማላቅና በርሱ ወደማመን በመጣራት ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ነው። ሁለተኛው: ለመፅሀፉ ታማኝ (ተቆርቋሪ) መሆን ነው። እርሱም የተከበረው ቁርአን ነው። ይህም ቁርአን የአላህ ንግግር መሆኑን፣ የመጨረሻ መፅሀፉ መሆኑን፣ ከቁርአን በፊት የነበሩትን ሁሉንም ህግጋት የሻረ መሆኑን ማመን፤ እናልቀዋለን፣ በአግባቡ እናነበዋለን፣ ግልፅ በሆኑ ህግጋቶቹ እንተገብራለን፣ አሻሚ ትርጓሜ ባላቸው አንቀጾች እናምናለን፣ ቁርአንን አጣመው ከሚተረጉሙ ሰዎች ስለቁርአን እንከላከላለን፣ በምክሮቹ እንገሰፃለን፣ እውቀቶቹን እናሰራጫለን፣ ወደርሱም ጥሪ እናደርጋለን። ሶስተኛው: ለመልክተኛው ሙሐመድ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ማለት እርሳቸው የመጨረሻ መልክተኛ መሆናቸውን በማመን፣ ይዘውት የመጡትን እውነት ብለን በመቀበል፣ ትእዛዛቸውን በመፈፀም፣ ክልከላቸውንም በመራቅ፣ እርሳቸው ይዘውት በመጡት መልኩ ካልሆነ በቀር አላህንም ባለማምለክ ሐቃቸውን ማላቅ፣ ማክበር፣ ጥሪያቸውን ማሰራጨት፣ ሸሪዓቸውን ማስፋፋትና እርሳቸው ላይ የሚነዛን ብዥታንም ውድቅ ማድረግ ነው። አራተኛው: ለሙስሊም መሪዎች ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ማለት: በሐቅ ላይ በማገዝ፣ በጉዳያቸው ባለመቀናቀን፣ አላህን በታዘዙበት ጉዳይም ትእዛዛቸውን በመስማትና በመታዘዝ ነው። አምስተኛው: ለሙስሊሞች ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ማለት: ለነርሱ በጎ በመዋል፣ ጥሪ በማድረግ፣ በነርሱ ላይ ጉዳት ከማድረስ በመቆጠብ፣ ለነርሱ መልካሙን በማሰብ፣ በመልካምና አላህን በመፍራት ላይም ከነርሱ ጋር በመተጋገዝ ነው።فوائد الحديث
ለሁሉም (ቅን/ ታማኝ) መሆን መታዘዙን እንረዳለን።
በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ (ቅን/ ታማኝ) የመሆን ደረጃ የላቀ መሆኑን እንረዳለን።
የእስልምና ሃይማኖት እምነቶችን፣ ንግግሮችንና ተግባራቶችን ያጠቀለለ መሆኑን እንረዳለን።
ከታማኝነት መካከል አንዱ ቅንነቱ ለተገባው አካል ከማታለል ነፍሳችንን ማፅዳትና ለሱ መልካምን መፈለግ ነው።
መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድን ነገር በጥቅሉ አውስተው ከዚያም መዘርዘራቸው የሳቸውን የማስተማር ብቃታቸው ውበትን ይጠቁማል።
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለአላህ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ጀምረው ከዚያም ለመጽሐፉ ከዚያም ለመልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዚያም ለሙስሊም መሪዎች ከዚያም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) በመሆን ማጠቃለላቸው የትኛውም ነገር እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ጉዳይ ሊጀመር እንደሚገባው እንረዳለን።
