إعدادات العرض
ጀነት ውስጥ (የጀነት ሰዎች) በየጁሙዓው የሚሄዱባት ሱቅ አለች።
ጀነት ውስጥ (የጀነት ሰዎች) በየጁሙዓው የሚሄዱባት ሱቅ አለች።
ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: «ጀነት ውስጥ (የጀነት ሰዎች) በየጁሙዓው የሚሄዱባት ሱቅ አለች። በስተሰሜን ንፋስ ትነፍስና ፊታቸውንና ልብሳቸውን ትገርፋለች። (በዚህም) ውበትና ቁንጅናን ይጨምራሉ። ውበትና ቁንጅናቸው ጨምሮም ወደ ሚስቶቻቸው ይመለሳሉ። ሚስቶቻቸውም እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! ከኛ ከተለያቹ በኋላ ውበትና ቁንጅናችሁ ጨምሯል።" እነርሱም ለሚስቶቻቸው "በአላህ እንምላለን! እናንተም ከኛ ከተለያችሁ በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Kurdî Nederlands Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી Magyar ქართული Hausa Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጀነት ውስጥ የጀነት ሰዎች የሚሰባሰቡበትና መሸጥና መግዛት ሳይጠበቅባቸው የፈለጉትን ነገር የሚወስዱበት ቦታ እንዳለ ተናገሩ። ወደዚህም ስፍራ በየሳምንቱ ይመጣሉ። በሰሜን አቅጣጫ ንፋስ ትነፍስና ፊታቸውንና ልብሳቸውን ታንቀሳቅሳለች። በዚህም ውበትና ቁንጅና ይጨምራሉ። ውበትና ቁንጅና ጨምረውም ወደ ሚስቶቻቸው ይመለሳሉ። ሚስቶቻቸውም ለነርሱ እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! ከኛ ከተለያችሁ በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።" እነርሱም ለሚስቶቻቸው እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! እናንተም ከተለያየን በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።"فوائد الحديث
የጀነት ሰዎች ውበትና ቁንጅና እንደሚጨምሩ መገለፁን እንረዳለን።
ሐዲሦቹ የሰው ልጅ ወደዚህች ሀገር የሚዳረስበት ለሆነው መልካም ስራ እንዲጓጓ ያደርጋሉ።
ሐዲሡ ላይ የሰሜን አቅጣጫ ንፋስ ተለይቶ የተጠቀሰው ዐረቦች ዘንድ መልካምንና ዝናብን ይዛ በመምጣት የምትታወቅ ምርጥ ንፋስ ስለሆነች ነው።
ስለጀነትና ፀጋዎቿ በማነሳሳት ወደ አላህ በመጣራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
التصنيفات
የጀነትና እሳት ባህሪዎች