إعدادات العرض
ዉዱእን አዳርሰህ አድርግ። በጣቶችህ መካከል ፈልፍል። ፆመኛ እስካልሆንክ ድረስም አፍንጫህ ውስጥ ውሃ ስትከት በደንብ አስገባ።" አሉኝ።
ዉዱእን አዳርሰህ አድርግ። በጣቶችህ መካከል ፈልፍል። ፆመኛ እስካልሆንክ ድረስም አፍንጫህ ውስጥ ውሃ ስትከት በደንብ አስገባ።" አሉኝ።
ለቂጥ ቢን ሰቢራህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንዲህ አሉ: «ወደ አላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተላኩ የበኒ አልሙንተፊቅ ወይም በበኒ አልሙንተፊቅ ልዑክ ውስጥ ነበርኩ። የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ስንደርስ በቤታቸው አላገኘናቸውም ነበር። የአማኞች እናትን ዓኢሻን አገኘን። በስጋና ዱቄት የሚሰራ (ኸዚራ) የሚባል ምግብ እንዲሰራልን አዘዘች። ለኛም ተሰራልን። በጎድጓዳ ሳህንም ተምር መጣልን። ከዚያም የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መጥተው እንዲህ አሉን "የሚቀመስ ነገር አገኛችሁ?" ወይም "የሚቀመስ ነገር ታዘዘላችሁ?" እኛም "አዎ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልን። እኛ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተቀምጠን ሳለ የርሳቸው እረኛ ፍየሎቹን ወደ ማደሪያቸው ያስገባ ጀመር። ከርሱ ጋር የምትጮህ ግልገል ነበረች። እርሳቸውም "እከሌ ሆይ! አላራባህምን?" አሉት። እርሱም "ግልገል ናት።" አላቸው። እርሳቸውም "በርሷ ቦታ አንድ ፍየል እረድልና!" አሉት። ቀጥለውም "ለናንተ ብለን የምናርድላችሁ አድርጋችሁ እንዳታስቡ። እኛ መቶ ፍየል አለን። ከመቶ እንዲጨምር ስለማንፈልግ እረኛው አንድ ሲያራባ በርሷ ቦታ አንድ እናርዳለን።" አሉ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ምላሷ ላይ ችግር ያለባት ሚስት አለችኝ። ምን ይሻለኛል?" ብዬ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም "እንደዛ ከሆነ ፍታት" አሉኝ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሷ ከኔ ጋር የቆየ ቁርኝት አላት። ከርሷም ልጆች አሉኝ።" አልኳቸው። እርሳቸውም "ምከራት! ውስጧ መልካምነት ካለ ትታዘዝሃለች። ሚስትህን የባሪያ አመታት እንዳትመታ።" አሉኝ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለ ዉዱእ ንገሩኝ።" አልኳቸው። እርሳቸውም "ዉዱእን አዳርሰህ አድርግ። በጣቶችህ መካከል ፈልፍል። ፆመኛ እስካልሆንክ ድረስም አፍንጫህ ውስጥ ውሃ ስትከት በደንብ አስገባ።" አሉኝ።»
الترجمة
العربية Bosanski English فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt Español Kurdî Magyar ქართული සිංහල Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Hausa Português मराठी دری বাংলা ភាសាខ្មែរالشرح
ለቂጥ ቢን ሰቢራህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ከህዝቦቹ ተመርጦ ከሌሎች ጋር ወደ አላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተላኩ የበኒ አልሙንተፊቅ ልዑክ ውስጥ እንደነበረ ተናገረ። እንዲህም አለ: በቤታቸው አላገኘናቸውም ነበር። የአማኞች እናትን ዓኢሻን -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና - አገኘን። በስጋና ዱቄት የሚሰራ (ሐሳእ) የሚባል ምግብ እንዲሰራልን አዘዘች። ለኛም ተሰራልን። በጎድጓዳ ሳህንም ተምር መጣልን። ከዚያም የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መጥተው እንዲህ አሉን "የሆነ ምግብ ቀረበላችሁ?" እኛም "አዎ" አልን። ለቂጥ እንዲህ አለ: እኛ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተቀምጠን ሳለ የነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እረኛ ፍየሎቹን ወደ ማደሪያቸው ሊያስገባ እየነዳ አመጣቸው። ከርሱ ጋርም የምትጮህ የፍየል ግልገል ነበረች። እርሳቸውም "አላራባህምን?" አሉት። እርሱም "ሴት ግልገል ናት።" አላቸው። እርሳቸውም "በርሷ ቦታ አንድ የደረሰች ፍየል እረድልና!" አሉት። ቀጥለውም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "ለናንተ ብለን ተጨናንቀን የምናርድላችሁ አድርጋችሁ እንዳታስቡ። እኛ መቶ ፍየል አለን። ከመቶ እንዲጨምር ስለማንፈልግ አንድ አዲስ ግልገል ሲወለድልን በርሷ ቦታ አንድ እናርዳለን።" አሉ። ለቂጥም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ምላሷ ላይ ጣጣ ያለባት አስከፊ ምላስ ያላት ሚስት አለችኝ። ከርሷ ጋር ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብዬ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም "እንደዛ ከሆነ ፍታት" አሉኝ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሷ ከኔ ጋር የቆየ ቁርኝት አላት። ከርሷም ልጆች አሉኝ።" አልኳቸው። እርሳቸውም "ምከራት! ውስጧ መልካምነት ካለ ምክርህን ትቀበልሃለች። ካልተቀበለች የማያቆስል ምት ምታት እንጂ ሚስትህን የባሪያ አመታት እንዳትመታ።" አሉኝ። ለቂጥም ቀጥሎ እንዲህ አላቸው "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለ ዉዱእ ንገሩኝ።" አላቸው። እርሳቸውም "ዉዱእህን ስታደርግ ዉዱእን አዳርሰህ አድርግ። ለሁሉም አካላትህ ሐቁን ስጥ። የዉዱእን ግዴታና ሱና ምንም አትተው። በእጅና እግር ጣቶችህ መካከል ከፋፍትና ፈልፍል። ውሃው ወደ ውስጥህ እንዳይገባ ጾመኛ እስካልሆንክ ድረስ አፍንጫህ ውስጥ ውሃ ስትስብ በደንብ አስገባ።" አሉኝ።فوائد الحديث
እንግዳን መንከባከብ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
ዉዱእን አዳርሶ ማድረግ ሁለት አይነት ነው። 1: ግዴታ የሆነ ማዳረስ ነው። ይሀውም እርሱን ካላሟላ በቀር ዉዱኡ የማይሞላበት የሆነ ማዳረስ ነው። በዚህም የሚፈለገው የዉዱኡን አካላት አዳርሶ ማጠብ ነው። 2 ተወዳጅ የሆነ ማዳረስ ነው። ይሀውም ያለርሱም ዉዱኡ የሚበቃለት ነው። በዚህም የሚፈለገው ከግዴታው ትጥበት በላይ የሚታጠበው ሁለተኛና ሶስተኛ ትጥበት ነው። ይህም ተወዳጅ ተግባር ነው።
እጆችንና እግሮችን በሚታጠብ ወቅት ጣቶችን መፈልፈል እንደሚወደድ እንረዳለን። ጣቶችን መፈልፈል ሲባል ውሃን በመካከላቸው እንዲደርስ ማድረግ ማለት ነው።
ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መልሳቸውን ስለ አንዳንድ የዉዱእ ሱናዎች ያደረጉለት ጠያቂው መሰረታዊ የዉዱእ እውቀት ስለነበረው ነው።"
ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሁለንተናዊ ውብ ማንነት መካከል ለሌሎች ስሜት መጨነቃቸውና ሞራላቸውን መጠበቃቸው አንዱ ነው።
ይህ ሐዲሥ በዉዱእ ወቅት መጉመጥመጥ ግዴታ መሆኑን ይጠቁማል።
ይህ ሐዲሥ ፆመኛ እስካልሆነ ድረስ ውሃን አፍንጫ ውስጥ በደንብ ስቦ ማስገባት እንደሚወደድ ይጠቁማል። ፆመኛ ከሆነ ግን ውሃን ወደ አፍንጫው ስቦ ሲያስገባ ከአፍንጫው አልፎ ወደ ጉሮሮው በመድረስ ፆሙን ሊያበላሽበት ስለሚችል አይወደድም።
ይህ ሐዲሥ የሰለመ ሰው ሁሉ መሰደድ ግዴታ እንዳልሆነበት ያስረዳናል። በኒልሙንተፊቆችና ሌሎችም አልተሰደዱም ይልቁንም ልዑኮቻቸውን ነው የላኩት። ልክ እንደዚሁ ሃይማኖቱን በግልፅ መተግበር የሚችልበት ቦታ የሆነ ሰው መሰደድ ግዴታው አይሆንበትም።
التصنيفات
የዉዹእ ሱናና ስነ-ስርዓት