ባለረዥም ፀጉር ሁኖ ቀያይ መስመር ያለበትን ጥቁር አለባሽ ልብስ የሚያምርበት ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የበለጠ እጅግ ውብ ሰው አልተመለከትኩም።

ባለረዥም ፀጉር ሁኖ ቀያይ መስመር ያለበትን ጥቁር አለባሽ ልብስ የሚያምርበት ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የበለጠ እጅግ ውብ ሰው አልተመለከትኩም።

ከበራእ- አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ባለረዥም ፀጉር ሁኖ ቀያይ መስመር ያለበትን ጥቁር አለባሽ ልብስ የሚያምርበት ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የበለጠ እጅግ ውብ ሰው አልተመለከትኩም። ፀጉራቸው ትከሻቸውን ይመታ ነበር። በሁለቱ ትከሻዎቻቸው መካከል መራራቅ አለ። ረጅምም አጭርም አይደሉም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

በራእ ቢን ዓዚብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የበለጠ ከርዝመቱ የተነሳ ፀጉሩ ትከሻው ድረስ የደረሰና ቀያይ መስመሮች ያሉበት ጥቋቁር ሽርጥና ኩታ የለበሰ አንድም እጅግ ውብ ሰው አልተመከትኩም ብለው ተናገሩ። በተጨማሪም ከርሳቸው አካላዊ ተፈጥሮ መካከል በሁለቱ ትከሻዎቻቸው መካከል መራራቅ እንዳለ፣ ደረታቸው ሰፊና ቁመታቸው አጭርም ረጅምም ሳይሆን መካከለኛ ቁመት እንደሆነ ተናገሩ።

فوائد الحديث

እንደ ፀጉር ማማር፣ የደረት መስፋት፣ ያማረ ተክለ ቁመናና ከዚህ ውጪም ያሉ ጥቂት የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ውብ የሆኑን ውጫዊ ባህሪያቶች ተብራርተው እናያለን።

የተከበሩት ሶሓቦች (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያላቸውን ውዴታ እንመለከታለን። ውዴታቸው ከነርሱ በኋላ ለመጡት ትውልዶች ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) አካላዊና ውስጣዊ ባህሪያትና ሁለንተናዊ መገለጫ እስከመተረክና እስከማስተላለፍ የደረሰ ነበር።

التصنيفات

አካላዊ ባህሪያቸው, የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ልብስ