إعدادات العرض
‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።›
‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።›
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም: ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።› አሏት። እርሷም ‹እታገሳለሁ።› ብላ እንዲህም አለች: ‹እኔ እገላለጣለሁኝ። እንዳልገላለጥ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።"»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt Kurdî Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Hausa Português मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ኢብኑ ዐባስ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ለዐጧእ ቢን አቢረባሕ እንዲህ አሉ: "የጀነት ነዋሪ የሆነችን ሴት አላሳይህምን?" ዐጧእም "እንዴታ!" አለ። ኢብኑ ዐባስም እንዲህ አሉ: "ይህቺ ሐበሻዊት ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: "የሚጥል በሽታ ስላለብኝ ይጥለኝና እገላለጣለሁኝ። ታዲያ እኔ ሳላውቀው ከሰውነቴ የተወሰነው ክፍል ይገለጣል። አላህ ጤናን እንዲለግሰኝ ለምኑልኝ።" እርሳቸውም እንዲህ አሏት: "ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለልሽ። ከፈለግሽ ደግሞ አላህ ጤናን እንዲሰጥሽ እለምንልሻለሁኝ።" እርሷም እንዲህ አለች: "እንዲህ ከሆነ እታገሳለሁኝ። አክላም "ስወድቅ እንዳልገላለጥ ግን አላህን ይለምኑልኝ።" አለች። እርሳቸውም አላህን ለመኑላት።فوائد الحديث
በዱንያ በሚያጋጥሙ መከራዎች ላይ መታገስ ጀነትን ያስወርሳል።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የሚጥል በሽታ የተሟላን ምንዳ እንደሚያስመነዳ ይጠቁማል።"
ሴት ሶሓቦች (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) የነበራቸውን ሀፍረትና ጥብቅነት እንዲሁም ለመሸፈን የነበራቸውን ጥረት እንረዳለን። ይህቺ ሴት አብዝታ ትፈራ የነበረው ጉዳይ ከሰውነቷ አንዳች አካል እንዳይገለጥባት ነበር።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ነፍሱ አቅም እንዳላት የተረዳና በጠንካራው ትእዛዝ ለመዘውተር ያልደከመ ሰው የተግራራውን ትእዛዝ ከመተግበር ይልቅ ጠንካራውን ትእዛዝ መተግበሩ ይበልጥለታል።"
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በሽታዎችን ሁሉ በዱዓ፣ ወደ አላህ በመጠጋት ማከም በመድሓኒቶች ከመፈወስ የበለጠ ፈዋሽና ጠቃሚ እንደሆነ፣ የዱዓ ተፅእኖና የሚፈጥረው አካላዊ መነቃቃትም መድሃኒቶች ከሚፈጥሩት ተፅእኖ እጅግ የላቀ እንደሆነ እንረዳለን። ነገር ግን ይህ ስኬታማ የሚሆነው ሁለት ነገሮች ሲሟሉ ነው: የመጀመሪያው የሚፈለገው ከታማሚው ሲሆን እርሱም: በትክክል እድናለሁኝ የሚል ሃሳብ መሰነቅ ነው። ሁለተኛው: ከሚያክመው ሰው የሚፈለግ ሲሆን: ወደ አላህ የዞረበት ጥንካሬና ቀልቡ አላህን በመፍራትና በአላህ በመመካት የበረታ መሆኑ ነው።" አላህ የበለጠ አዋቂ ነው።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ህክምናን መተውም እንደሚፈቀድ ይጠቁማል።"