ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ላደረገ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።

ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ላደረገ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።

የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አንዲት ሴት ልትለምነኝ መጣች። እኔ ዘንድም ከአንድ ተምር ውጪ አላገኘችም። እርሱንም ስሰጣት ለሁለት ሴት ልጆቿ ሁለት ቦታ ከፋፍላ ሰጠች። ከዚያም ተነስታ ሄደች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኔ ዘንድ ሲገቡ ሁኔታውን ነገርኳቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ላደረገ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአማኞች እናት የሆነችው ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) እንዲህ በማለት ተናገረች: ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አንዲት ሴት እነርሱን ይዛ የሚበላ ነገር እንድትሰጣት ልትለምናት መጣች። ዓኢሻም ከአንድ ተምር ውጪ አላገኘችም። እርሱንም ስትሰጣት ለራሷ ምንም ሳትበላ ለሁለት ሴት ልጆቿ ሁለት ቦታ ከፋፍላ ሰጠች። ከዚያም ተነስታ ሄደች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷ ዘንድ ሲገቡ ሁኔታውን ነገረቻቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ያደረገ፣ በስነስርዓት ያነፃቸው፣ ያለበሳቸውና በዚህም ላይ የታገሰ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።"

فوائد الحديث

ሴቶችን መንከባከብና ለነርሱ መልካም ለማድረግ መልፋት ከእሳት የሚያርቁ ከሆኑት በላጭ መልካም ስራዎች መካከል አንዱ ነው።

የሰው ልጅ ትንሽ ብትሆን እንኳ በሚችለው መመፅወቱ እንደሚወደድለት እንረዳለን።

ወላጆች ለልጆቻቸው ያላቸውን የጠና ርህራሄ እንመለከታለን።

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤቶች የነበራቸውን ሁኔታ ተገልጾ እናየዋለን። የርሳቸው ሲሳይ ለቤተሰባቸው ብቻ የሚበቃ ነበር።

ሌላውን ማስቀደም ያለው ደረጃ መገለፁ። ይህ ባህሪ የአማኞች ባህሪ ነው። ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) ይህቺን ሴትና ልጆቿን ከራሷ በላይ አስቀደመቻቸው። ይህም ተምሩን በዚህ ደረጃ በጣም እየፈለገችውም መስጠቷ የርሷን ቸርነትና ደግንት ይጠቁማል።

ሴቶችን መውለድ ፈተና ተብሎ የተጠራው እነርሱን ማሳደግ አድካሚና ከባድ ስለሆነ ወይም አንዳንድ ሰዎች ሴት ሲወለድ ስለሚጠሉ ወይም በብዛት ለነርሱ የሚሆን የገቢ ምንጭና መተዳደሪያ ስለማይገኝ ነው።

እስልምና የተወገዘ የድንቁርና ዘመን ባህልን ከስሩ መናዳቸውን እንረዳለን። ከነዚህም መካከል አንዱ ሴቶችን በመንከባከብ አደራ ማለቱ ነው።

በሌሎች ዘገባዎች እንደመጣው አንዲት ሴት ልጅ ብቻ እንኳ ብትሆን ይህ ሐዲሡ ላይ የተጠቀሰውን ምንዳ ታስገኛለች።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር, የፈቃደኝነት ምፅዋት (ሶደቃ)