إعدادات العرض
ምስጉን ስነ-ምግባር
ምስጉን ስነ-ምግባር
1- አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።
2- አላህ ሁሉም ነገር ላይ መልካምነትን ጽፏል፤
3- ሰዎች ከቀደምት ነቢያት ካገኟቸው ቃላት መካከል ካላፈርክ የፈለግከውን ስራ! የሚለው አንዱ ነው።
4- በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውንም የጠላኸው ነገር ነው።
5- አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።
6- ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።
7- ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን
8- አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል።
9- አትቆጣ!
10- ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው።
11- ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው መልካምን ተነፍጓል።
12- ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።
13- ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።
14- ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።
15- በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!
16- ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።
19- በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና።
20- ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።
21- 'አላህ ጥንቁቅ፣ (ከሰዎች) የተብቃቃና ድብቅ የሆነን ባሪያ ይወዳል።'
22- 'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'
23- በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።
24- 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'
25- ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'
27- ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።
28- አንድ ባሪያ የአንድን ባሪያ ነውር በዱንያ አይሸፍንም፤ የትንሳኤ ቀን አላህ ነውሩን የሚሸፍንለት ቢሆን እንጂ።
29- በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውን የጠላኸው ነገር ነው።" አሉኝ።
30- ሰዎች ከቀደምት ነቢያት ካገኟቸው ቃላት መካከል ካላፈርክ የፈለግከውን ስራ! የሚለው አንዱ ነው።
31- አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።
32- የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።
33- ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።
34- ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።
40- አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ።
41- ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው።
43- እኔ የተላኩት መልካም ስነምግባርን ላሟላ ነው።
