إعدادات العرض
በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።
በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።
የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆነችው ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు မြန်မာ ไทย Deutsch 日本語 پښتو অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە Kiswahili தமிழ் دری Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda नेपाली Српски Wolof Soomaali Moore Українська Български Azərbaycan ქართული тоҷикӣ bm Oromoo Македонскиالشرح
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በንግግርም ይሁን በተግባር ገራገርነት፣ ለስላሳነትና እርጋታ ነገሮች ላይ ውበት፣ ምሉዕነትና ማማር የሚጨምር እንዲሁም ይህንኑ ባህሪ የተላበሰ ሰውም ጉዳዩን ለማሳካት የተገባ እንደሆነ ገለፁ። ገራገር (ለስላሳ) አለመሆን ደግሞ ነገሮችን ያነውራቸዋልም አስቀያሚ ያደርጋቸዋልም፤ ስለዚህም ባለቤቱ አላማውን እንዳያገኝ ይከለክለዋል። ካገኘም በችግር ነው የሚያገኘው።فوائد الحديث
ለስላሳ ባህሪን በመላበስ ላይ መበረታታቱን ተረድተናል።
ገራገርነት (ልስላሴ) ሰውን ያስውባል። ገራገርነት በዱንያም (ልስላሴ) በአኺራም የሚገኙ ሁሉም መልካም ጉዳዮችን ለማግኘት ምክንያት ነው።
التصنيفات
ምስጉን ስነ-ምግባር