إعدادات العرض
ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'
ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለጌ (ጸያፍ) አልነበሩም፣ ጸያፍ ቃላትም አይናገሩም። እንዲህም ይሉ ነበር: ' ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം မြန်မာ ไทย Deutsch 日本語 پښتو অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands తెలుగు Kiswahili தமிழ் دری Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda नेपाली Српски Wolof Soomaali Moore Українська Български Azərbaycan ქართული тоҷикӣ bmالشرح
ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መካከል ፀያፍ መናገር ወይም ፀያፍ ድርጊት አይገኝም ነበር። ትዝም አይላቸው። እሳቸው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የላቀ ስነምግባር ባለቤት ነበሩ። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ዘንድ ከናንተ መካከል በላጩ መልካምን በመለገስ፣ ፊቱን በመፍታት፣ ሰውን ከማወክ በመቆጠብና የነሱን ክፋት በመቻል እንዲሁም ሰዎች ጋር ባማረ መልኩ በመኗኗር ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።"فوائد الحديث
አንድ አማኝ ከፀያፍ ንግግርና ከመጥፎ ተግባር ሊርቅ እንደሚገባው፤
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ምሉዕ መሆኑንና ከሳቸው መልካም ስራና ምርጥ ንግግር እንጂ ሌላ እንደማይመነጭ፤
መልካም ስነምግባር የሽቅድድም መድረክ መሆኑን እንረዳለን። የቀደመ ምርጥ አማኝና ኢማኑ የሞላ ይሆናል።
التصنيفات
ምስጉን ስነ-ምግባር