إعدادات العرض
ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው።
ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው።
ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፡ «"ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው። ወደኔ የተጠላውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ከኔ እጅግ የራቀው እውነትን ለመቀልበስ እየተጣጣረ የሚያወራ፤ ለአንደበተ ርቱእነት ንግግር የሚያበዛና ሙተፈይሂቆች ናቸው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እውነትን ለመቀልበስ እየተጣጣረ የሚያወራንና ለአንደበተ ርቱዕነት ንግግር የሚያበዛን አውቀናል። መተፈይሂቆች እነማን ናቸው?" አሉ። እርሳቸውም "ኩራተኞች ናቸው።" አሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල ئۇيغۇرچە Kurdî தமிழ் অসমীয়া Nederlands Kiswahili Hausa ไทยالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: ዱንያ ውስጥ ወደኔ ተወዳጁ፤ የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሆነው ስነምግባሩ ያማረ ነው። ዱንያ ውስጥ ወደኔ የተጠላው የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ከኔ የራቀው መጥፎ ስነምግባር ያለው፤ (ሠርሣሮች) ከእውነት ለመውጣት ከአቅሙ በላይ እየተጣጣረ ንግግር የሚያበዛ፤ (ሙተሸዲቆች) ያለምንም ጥንቃቄ አንደበተ ርቱዕ ለመባልና ንግግሩን ለማላቅ ንግግሩን የሚያሰፋ፤ እና (ሙተፈይሂቆች) ናቸው። ሶሐቦችም የአላህ መልክተኛ ሆይ! "ሠርሣሮች" እና "ሙተሸዲቆች"ን አውቀናል። "ሙተፈይሄቆች" ማን ናቸው? አሉ። እርሳቸውም: "ኩራተኞች፣ ንግግራቸውን በማስፋትና በንግግራቸው አፋቸውን በመክፈት በሰዎች ላይ የሚያፌዙ ናቸው።" አሉ።فوائد الحديث
መልካም ስነምግባር የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ውዴታንና የትንሳኤ ቀን ወደርሳቸው መቅረብን ከሚያመጡ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው።
መልካም ስነምግባር ሰዎች እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው። መጥፎ ስነምግባር ደግሞ በተቃራኒ ነው።
ስነምግባርን በማሳመር፤ በመተናነስ፣ ጨካኝ ባለመሆንና ያለአቅም ባለመጣጣር ላይ መነሳሳቱን ተረድተናል።
ማብዛትን፣ ኩራትን፣ ልቆ መታየትን፣ ከአቅም በላይ መጣጣርን አስቦ ከመናገር መከልከሉን እንረዳለን።
التصنيفات
ምስጉን ስነ-ምግባር