አንተ ውስጥ ሁለት አላህ የሚወዳቸው ነገሮች አሉ። እነርሱም አስተዋይነትና መረጋጋት ናቸው።

አንተ ውስጥ ሁለት አላህ የሚወዳቸው ነገሮች አሉ። እነርሱም አስተዋይነትና መረጋጋት ናቸው።

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለአሸጅ ዐብዲል ቀይስ እንዲህ አሉ: "አንተ ውስጥ ሁለት አላህ የሚወዳቸው ነገሮች አሉ። እነርሱም አስተዋይነትና መረጋጋት ናቸው።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የዐብዱል ቀይስ የሚባል ጎሳ መሪ ለሆነው ለሙንዚር ቢን ዓኢዝ አሸጅ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንዲህ አሉት: አንተ ውስጥ አላህ የሚወዳቸው ሁለት ባህሪያት አሉ። እነርሱም: አስተዋይነት፣ ማረጋገጥ፣ እርጋታና አለመቸኮል ናቸው።

فوائد الحديث

አስተዋይነትንና እርጋታን በመላበስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ነገሮችን በማረጋገጥና የሚያስከትሉትን ነገር በመመልከት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

አስተዋይነትና እርጋታ ምስጉን ከሆኑ ባህሪያቶች መካከል ነው።

ሰዎች አላህ በተፈጥሮ ላጎናፀፋቸው ምስጉን ስነምግባር አላህን ማመስገን እንደሚገባቸው እንረዳለን።

አሸጅ ማለት ፊት ላይ ወይም ጭንቅላት ላይ ወይም ግንባር ላይ የቆሰለ ማለት ነው።

التصنيفات

አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል, ምስጉን ስነ-ምግባር