إعدادات العرض
ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።
ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።"
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ ไทย Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली Malagasy Italiano or ಕನ್ನಡ Oromoo Română Soomaali Српски Wolof Українська Moore Azərbaycan ქართული Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚያ ለሌሎች የሚያዝኑ አዛኙ ጌታ ሁሉን ነገር በሰፋው እዝነቱ እንደሚያዝንላቸው ገለፁ። ይህም ከሰሩት ጋር የገጠመ ምንዳ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው በምድር ላይ ለሚኖር ለሰውም፣ ለእንስሳም፣ ለበራሪም ሆነ ለሌላ ማንኛውም አይነት ፍጡር ባጠቃላይ ማዘንን አዘዙ። የዚህ ምንዳም ከሰማያቱ በላይ ያለው አላህ ያዝንላቹሀል።فوائد الحديث
የእስልምና ሀይማኖት የእዝነት ሀይማኖት ነው። የኢስላም ሁለመናው አላህን በመታዘዝና ለፍጡራን መልካም በማድረግ ላይ የቆመ ነው።
የላቀው አላህ በእዝነት ባህሪ የሚገለፅ ነው። ጥራት የተገባው አላህ አዛኝ ሩህሩህ ነው። ወደ ባሮቹ እዝነቱን የሚያደርስ ጌታ ነው።
ምንዳ የሚመነዳው በስራው አይነት ነውና ለአዛኞች አላህ ያዝንላቸዋል።