እኔ የተላኩት መልካም ስነምግባርን ላሟላ ነው።

እኔ የተላኩት መልካም ስነምግባርን ላሟላ ነው።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እኔ የተላኩት መልካም ስነምግባርን ላሟላ ነው።"

[ሐሰን ነው።]

الشرح

አላህ ዐዘ ወጀል ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የላካቸው መልካምና በላጭ ስነምግባርን ሊሞሉ እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከርሳቸው በፊት የነበሩ መልክተኞች ላስተላለፉት የመልካምነት ጥሪ አሟይና ዐረቦች የነበሩበትን መልካም ስነምግባር ሊሞሉ ነው የተላኩት። ዐረቦች መልካምን የሚወዱና መጥፎን የሚጠሉ፣ የክብር፣ የቸርነትና የታላቅነት ባለቤት ነበሩ። ታዲያ ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዐረቦች የጎደላቸውን ስነምግባር ሊሞሉ ተላኩ። ለምሳሌ በዘር መኩራራት፣ ኩራት፣ ድሃን መናቅና ከዚህም ውጪ የሚጎድላቸው ስነምግባሮች ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።

فوائد الحديث

በመልካም ስነምግባር ላይ መነሳሳቱንና የመልካም ስነምግባር ተቃራኒም መከልከሉን እንረዳለን።

በእስልምና ሸሪዓ ውስጥ መልካም ስነምግባር ያለው አንገብጋቢነት መገለፁንና እርሱም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች መካከል እንደሆነ እንረዳለን።

የጃሂሊያ ሰዎች ዘንድ ቅሪት መልካም ስነምግባሮች ነበሩ። ከነርሱም መካከል ቸርነት፣ ጀግንነትና ከዚህም ውጪ ያሉ ይጠቀሳሉ። እስልምናም ይህንን ስነምግባር ሊሞላ ነው የመጣው።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር