ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።

ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትክክለኛ ሀይል አካላዊ ሀይል ወይም ጉልበተኞችን የሚጥል ሳይሆን ብርቱና ሀይለኛ የሚባለው ቁጣው በሚበረታ ወቅት ነፍሱን የታገለና ያሸነፋት መሆኑን ገለፁ። ምክንያቱም ይህ ሰው ነፍሱን የመቆጣጠርና ሰይጣንን የማሸነፍ አቅም እንዳለው ይጠቁማልና።

فوائد الحديث

የቻይነትና ነፍስን በቁጣ ወቅት የመቆጣጠር ትሩፋትን እንረዳለን። ይህ ኢስላም ያነሳሳበት ከሆኑ መልካም ስራዎች መካከል አንዱ ነውና።

ነፍስን በቁጣ ወቅት መታገል ጠላትን ከመታገልም የበለጠ ከባድ መሆኑን እንረዳለን።

ጃሂሊዮች ለሀይለኝነት የሰጡትን ትርጓሜ ኢስላም ወደ ክቡር መገለጫ ስነ ምግባር መለወጡን እንረዳለን። ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ የነፍሱን ልጓም የተቆጣጠረ ነውና።

በግለሰብም ደረጃ ይሁን በማህበረሰብ ደረጃ ጉዳት ከማስከተሉ አኳያ ከቁጣ መራቅ እንደሚገባ እንረዳለን።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር, ምስጉን ስነ-ምግባር