إعدادات العرض
አማና (አደራ) የሌለው ሰው ኢማን የለውም፤ ቃልኪዳን የማያከብር የሆነ ሰው ሃይማኖት የለውም።
አማና (አደራ) የሌለው ሰው ኢማን የለውም፤ ቃልኪዳን የማያከብር የሆነ ሰው ሃይማኖት የለውም።
ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ ነቢይ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሳይሉን አንድም ኹጥባ አያደርጉም ነበር: "አማና (አደራ) የሌለው ሰው ኢማን የለውም፤ ቃልኪዳን የማያከብር የሆነ ሰው ሃይማኖት የለውም።"»
[Hasan/Sound by virtue of corroborating evidence] [አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Tiếng Việt Bahasa Indonesia Nederlands Kiswahili অসমীয়া English ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دری বাংলা Kurdîالشرح
አነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለው ተናገሩ: ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ኹጥባ ሲያደርጉ ወይም ሲመክሩ ሁለት ነገሮችን ሳይጠቅሱ የሚያልፉበት ጊዜ በጣም ጥቂት ጊዜያት ነው። የመጀመሪያው: አንድን አካል በገንዘብ ወይም በነፍስ ወይም በቤተሰብ ጉዳይ ነፍሱ ውስጥ ከዳተኝነት ያለችበት ሰው የተሟላ ኢማን የለውም። ሁለተኛው: ቃልኪዳንን የሚያፈርስ ሰው የተሟላ ሃይማኖት የለውም።فوائد الحديث
አደራን በመወጣት ላይና ቃልኪዳንን በመሙላት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። እነዚህን ሁለት ነገሮች ማፍረስ ኢማንን ያፈርሳል።
አደራን ከመካድና ቃልኪዳንን ከማፍረስ መከልከሉንና እነዚህን መፈፀምም ከትላልቅ ወንጀሎች እንደሆነ እንረዳለን።
ሐዲሡ በአላህና በባሪያው መካከል ያለንም ይሁን ፍጡራን እርስ በርሳቸው መካከል ያለውንም አደራ መጠበቅንና ቃልኪዳን ማክበርን ያካትታል።
التصنيفات
ምስጉን ስነ-ምግባር