إعدادات العرض
በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!
በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር!"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் دری Fulfulde Magyar ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan ქართული тоҷикӣ bm Македонски Ελληνικά ភាសាខ្មែរ Malagasy Oromoo Akanالشرح
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ እና በሚመለስበትና በስራው የሚመነዳበት በሆነው በመጨረሻው ቀን ያመነ ባሪያ ኢማኑ እነዚህን ጉዳዮችን በመፈፀም ላይ እንደሚያነሳሳው ገለፁ: የመጀመሪያው: መልካም መናገር ነው። በዚህ ውስጥ ሱብሓነላህ ማለት፣ ላኢላሃኢለላህ ማለት፣ በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል፣ በተጣሉ ሰዎች መካከል ማስማማት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ይህንን ካልፈፀመ ዝምታን ያዘውትር፣ ክፋቱን ይቆጥብ፣ ምላሱን ይጠብቅ። ሁለተኛ: ጉረቤትን ማክበር፡ ይህም እነሱን ባለማወክና ለነርሱ በጎ በማድረግ ነው። ሶስተኛ: ለመዘየር የመጣን እንግዳ መልካም በማናገር፣ ምግብ በማብላትና ይህን በመሳሰሉት ማክበር ነው።فوائد الحديث
በአላህና በመጨረሻው ቀን ማመን ለሁሉም መልካም ነገር መሰረት ነው። መልካም ተግባራትን በመፈፀም ላይም ያነሳሳል።
ከምላስ ወለምታ መከልከሉን እንረዳለን።
የኢስላም ሃይማኖት የአንድነትና የቸርነት ሃይማኖት መሆኑን እንረዳለን።
እነዚህ ጉዳዮች ከኢማን ክፍሎችና ምስጉን ከሆኑ ስነስርአቶች መካከል መሆናቸውን እንረዳለን።
ንግግር ማብዛት ወደሚጠላ ወይም ወደተከለከለ ነገር ይጎትታል። ሰላም የሚገኘው ከመልካም ውጪ ባለመናገር እንደሆነ እንረዳለን።
التصنيفات
ምስጉን ስነ-ምግባር