ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።

ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።

ከአቡ መስዑድ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "መንገድ ተቋርጦብኛልና የምጓጓዝበት እንስሳ ይስጡኝ?" አላቸው። እሳቸውም "የለኝም!" አሉት። ሌላ ሰውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ መጓጓዣ የሚሰጠውን እጠቁመዋለሁ!" አለ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "እኔ ግመሌ ስለጠፋች የሚያደርሰኝን አንድ መጓጓዣ ይስጡኝ!" አላቸው። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እሳቸው የሚሰጡት ምንም ነገር እንደሌለ ነገሩት። እሳቸው ዘንድ የነበረ አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ የሚሰጠውን ሰው እጠቁመዋለሁ።" አለ። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምፅዋት ፈላጊን ለሚመፀውተው አካል በመጠቆሙ ምክንያት ከሚመፀውተው ሰው ጋር በአጅር እንደሚጋራ ተናገሩ።

فوائد الحديث

ወደ መልካም ነገር መጠቆም መበረታታቱን ፤

መልካም በመፈፀም ላይ መቀስቀስ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እርስ በርስ እንዲተባበሩና እንዲዋሃዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ መሆኑን ፤

የአላህ ችሮታ ሰፊ መሆኑን ፤

ሀዲሱ ሁሉን የሚያካትት መርህ ስለሆነ በውስጡ ሁሉም መልካም ስራዎች የሚገቡ መሆኑን ፤

የሰው ልጅ የጠያቂን ፍላጎት ማሳካት ካልተመቻቸለት ለጠያቂው የሚያሳካለትን ሌላ አካል መጠቆም እንዳለበት እንረዳለን።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር