ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።

ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።

ከአቡ ደርዳእ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙስሊም ወንድሙ በራቀ ወቅት እንዳይወገዝ ወይም በርሱ ላይ መጥፎ እንዳይደርስበት በመከልከል ከሙስሊም ወንድሙ ክብር ለተከላከለ ሰው አላህ የትንሳኤ ቀን ቅጣትን ከሱ እንደሚከላከልለት ተናገሩ።

فوائد الحديث

የሙስሊሞችን ክብር የሚነካ ንግግር መናገር መከልከሉን፤

ምንዳ በስራ አምሳያ (ልክ) ነው። ከወንድሙ ክብር ለተከላከለ ሰው አላህም ከሱ ላይ እሳትን ይከላከልለታል።

ኢስላም በተከታዮቹ መካከል ወንድማማችነትና መረዳዳትን የሚያጠናክር እምነት መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት, ምስጉን ስነ-ምግባር