إعدادات العرض
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት
1- ስራዎች (ተቀባይነታቸው የሚለካው) በኒያ ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው የሚመነዳውም ባለመው ኒያ ልክ ብቻ ነው።
2- ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
3- እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ መልካም ነው። ከመልካም በቀርም አይቀበልም። አላህ መልክተኞችን ባዘዘው ነገር አማኞችንም አዟል።
4- አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።
5- አላህ ሁሉም ነገር ላይ መልካምነትን ጽፏል፤
6- ሰዎች ከቀደምት ነቢያት ካገኟቸው ቃላት መካከል ካላፈርክ የፈለግከውን ስራ! የሚለው አንዱ ነው።
9- አንዳችሁ ዝንባሌው ይዤ የመጣሁትን እስከሚከተል ድረስ አላመነም።
12- በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውንም የጠላኸው ነገር ነው።
13- ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።
14- 'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?
15- አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።
16- ትላልቅ ወንጀሎች፦ በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፣ ነፍስ ማጥፋትና የውሸት መሀላ ናቸው።
17- ‹ባሏ ለሞተባትና ለሚስኪን የሚለፋ ሰው ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ሰው አምሳያ ወይም ልክ ሌሊት እየሰገደ ቀኑን እንደሚፆም አምሳያ ነው›
19- እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'
20- ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።
21- በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።
22- በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።
23- በሁለት መንገጭላዎቹ መካከል እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያሉትን አካላት (ሊጠብቅ) ዋስትና ለገባልኝ እኔም ጀነትን ዋስትና እገባለታለሁ።
24- በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'
25- ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።
26- ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።
28- ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።
30- ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።
31- ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን
32- ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው።
33- ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
34- አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል።
35- አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።
36- ስራዎች የሚለኩት በኒያዎች (በሀሳብ) ብቻ ነው። ሁሉም ሰው የሚያገኘው ያሰበውን ነው።
37- አትቆጣ!
39- አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!
40- ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው።
41- ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው መልካምን ተነፍጓል።
42- ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።
43- በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።
44- አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና።
46- ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።
47- ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።
48- ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።
49- ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።
50- ለአንድ ሰው ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ሲገናኙ ይህም ይዞራል ያኛውም ይዞራል። ከሁለቱ ምርጡ ሰላምታ የሚጀምረው ነው።
53- ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።
54- አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!
55- በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!
56- ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።
57- ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።
61- 'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።
62- በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና።
63- ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ
64- ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።
65- ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።
67- አስር ጊዜ 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር' ያለ ሰው
68- አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል።
69- 'አላህ ጥንቁቅ፣ (ከሰዎች) የተብቃቃና ድብቅ የሆነን ባሪያ ይወዳል።'
70- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽቶን አይመልሱም ነበር።
71- 'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'
72- በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።
73- 'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'
74- 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'
75- ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'
76- 'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!
77- ከኔ በኋላ ለወንዶች ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።
80- አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'
81- ''ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊላህ ወላኢላሃ ኢለሏህ ወሏሁ አክበር' ማለቴ ፀሀይ የወጣችበት ክልል ሁሉ (ከሚሰጠኝ) የበለጠ ወደእኔ እጅግ ተወዳጅ ነው።'
82- በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።
83- 'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።)
84- ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።
85- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።
86- ዑመር ዘንድ ነበርንና እንዲህ አሉ: 'ከአቅም በላይ ከመጣጣር ተከልክለናል።'
88- አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ በል! በቀኝህ ብላ፣ ፊትህ ካለውም ብላ!
89- አንዳችሁ የበላ ጊዜ በቀኙ ይብላ። የጠጣም ጊዜ በቀኙ ይጠጣ። ሰይጣን የሚበላውም በግራው፤ የሚጠጣውም በግራው ነውና።
91- አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።
92- በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።" አሉ።
94- የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል
95- አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም
97- 'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤
98- ከፍ ያለው አላህ እንዲህ አለ: 'ሶላትን በኔና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፈልኩት። ለባሪያዬም የጠየቀው አለው።
99- ዐባስ ሆይ! የአላህ መልክተኛ አጎት ሆይ! አላህን በዱንያና በመጪው አለም ደህንነትን ጠይቀው።" አሉኝ።
