إعدادات العرض
አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው። አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ወደ ዉዱእ እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት እጁን ይጠብ! አንዳችሁ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።" የሙስሊም ዘገባ ላይ ደግሞ "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ሶስት ጊዜ ከማጠቡ በፊት ወደ እቃ ውስጥ አይንከረው! እርሱ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Kiswahili Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or नेपाली Malagasy Română Kinyarwanda తెలుగు Lietuvių Oromoo മലയാളം Nederlands Soomaali Shqip Српски Deutsch Українська ಕನ್ನಡ Wolof Moore ქართული Azərbaycan Magyarالشرح
ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዳንድ የጠሀራ ህግጋትን ገለፁ። ከነርሱም ውስጥ: የመጀመሪያው: ዉዱእ ያደረገ ሰው ውሀን ወደ አፍንጫው ውስጥ ስቦ ማስገባትና ድጋሚ ከአፍንጫው ማስወጣት ይገባዋል። ሁለተኛው: ሽንት ቤት ውስጥ ከርሱ የሚወጣውን ቆሻሻ ከውሃ ውጪ በድንጋይና በመሳሰሉ ነገሮች ማንፃትና ማስወገድ የፈለገ ሰው የመፀዳጃው ብዛት በጎዶሎ ቁጥር መሆን እንደሚገባ፤ ቢያንስ ሶስት ሲሆን ከፍተኛው ከርሱ የሚወጣውን ቆሻሻ የሚቆርጥና ቦታውን የሚያፀዳለት ያህል ነው። ሶስተኛው: ከሌሊት እንቅልፍ የነቃ ሰው እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና ነጃሳ አለመንካቱን ስለማይተማመን እንዲሁም ለሰው ልጅ የሚጎዳ ወይም ውሃውን የሚያበላሽ ነገርን ሰይጣን ወደ እጁ ተሸክሞ አምጥቶ ተጫውቶበት ሊሆንም ስለሚችል እጁን ከእቃው ውጪ ሶስት ጊዜ ሳያጥብ ዉዱእ ለማድረግም መዳፉን እቃ ውስጥ መክተት አይገባውም።فوائد الحديث
ዉዱእ ላይ ውሃን ወደ አፍንጫ መክተት ግዴታ ነው። እርሱም: ውሃን በትንፋሽ አማካኝነት ወደ አፍንጫ ውስጥ መክተት ሲሆን ልክ እንደዚሁ ውሃውን በትንፋሽ አማካኝነት ከአፍንጫው ማውጣትም ግዴታ ነው።
በጎዶሎ ቁጥር ማደራረቅ እንደሚወደድ እንረዳለን።
ከሌሊት እንቅልፍ በኋላ ሶስት ጊዜ ሁለት እጆችን ማጠብ እንደተደነገገ እንረዳለን።