إعدادات العرض
ዉዹእ
ዉዹእ
2- እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'
3- አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።
4- ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'
6- ተረከዞቻቸውን የዉዱእ ውሃ የማያስነኩ ከእሳት ወዮላቸው! ዉዱእን አዳርሳችሁ አድርጉ!
7- አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
8- የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው።
9- አንዳችሁ የተኛ ጊዜ በማጅራቱ ላይ ሸይጧን ሶስት ቋጠሮ ይቋጥራል። በየሁሉም ቋጠሮ ላይም ረጅም ሌሊት አለና ተኛ! እያለ ይመታል።
10- አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።
14- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር።
15- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።
16- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት ሁለት ጊዜ ዉዱእ አድርገዋል።
