ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'

ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'

ከዑሥማን ቢን ዐፋን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ውዱእን ሱናዎቹና አዳቦቹን ከመጠባበቅ ጋር ያደረገ ሰው ይህ ውዱኡ ወንጀሎቹ ከእጆቹና እግሮቹ ጣቶች ስር ጭምር እስኪወጡ ድረስ ወንጀሎቹ እንዲማሩና ሀጢአቶቹ እንዲረግፉ ከሚያደርጉ ምክንያቶቹ አንዱ መሆኑን እየነገሩን ነው።

فوائد الحديث

ውዱእን ሱናዎቹንና አዳቦቹን ተምሮ በመተግበር ላይ ትኩረት እንድናደርግ መነሳሳቱን እንረዳለን።

የውዱእን ትሩፋት እንረዳለን። ውዱእ ትናንሽ ወንጀሎችን የሚያስምር ነው። ትላልቅ ወንጀሎች ግን የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።

ወንጀሎች ከሰውነታችን እንዲወጡ ውዱእን ማሟላቱና ያለምንም ጉድለት ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደገለፁት መፈፀሙ መስፈርት ነው።

እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሰው ወንጀሎችን ማስማር ትላልቅ ወንጀሎችን በመራቅና ከርሱ ተውበት በማድረግ ላይ የተገደበ ነው። አላህ እንዲህ ብሏልና {ከእርሱ ከተከላችሁት ታላላቆቹን (ሀጢአቶች) ብትርቁ (ትናንሾቹን) ሀጢአቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን።} [አንኒሳእ:31]

التصنيفات

የዉዹእ ትሩፋት