إعدادات العرض
'አንዳችሁ ከሆዱ ውስጥ አንዳችን ነገር ያገኘ ጊዜ ከሆዱ አንዳች ነገር ወጥቷል ወይስ አልወጣም የሚለውን መለየት ካስቸገረው ድምፅ እስኪሰማ ወይም ሽታ እስኪያገኝ ድረስ (ሶላቱን አቋርጦ)…
'አንዳችሁ ከሆዱ ውስጥ አንዳችን ነገር ያገኘ ጊዜ ከሆዱ አንዳች ነገር ወጥቷል ወይስ አልወጣም የሚለውን መለየት ካስቸገረው ድምፅ እስኪሰማ ወይም ሽታ እስኪያገኝ ድረስ (ሶላቱን አቋርጦ) ከመስጂድ አይውጣ።'
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'አንዳችሁ ከሆዱ ውስጥ አንዳችን ነገር ያገኘ ጊዜ ከሆዱ አንዳች ነገር ወጥቷል ወይስ አልወጣም የሚለውን መለየት ካስቸገረው ድምፅ እስኪሰማ ወይም ሽታ እስኪያገኝ ድረስ (ሶላቱን አቋርጦ) ከመስጂድ አይውጣ።'"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Soomaali Shqip Српски Українська Wolof Tagalogالشرح
ሰጋጅ ከሆዱ ውስጥ አንዳች ነገር መውጣት አለመውጣቱን አስመልክቶ ከተጠራጠረ የፈስ ድምፅ በመስማት ወይም ጠረን በማሽተት ዉዱእ የሚያጠፋ ነገር መከሰቱን እርግጠኛ እስኪሆን ድረስ ዉዱእ ለመድገም ብሎ ሶላቱን አቋርጦ አይውጣ። የተረጋገጠ ነገር በጥርጣሬ አይበላሽምና። እሱ ዉዱእ እንደነበረው እርግጠኛ ነው፤ ዉዱእ ማጥፋቱ ግን አጠራጣሪ ነገር ነውና።فوائد الحديث
ይህ ሐዲሥ ከኢስላም መሰረቶች አንዱና ከፊቅህ መርሆዎች መካከል አንዱ መርህ ነው። እርሱም: የተረጋገጠ ነገር በጥርጣሬ አይወገድም ነው። መሰረቱ ተቃራኒው እስኪረጋገጥ ድረስ ሁሉም ነገር በነበረበት መጽናቱ ነው።
ጥርጣሬ በጠሀራ ላይ ተፅእኖ እንደማያሳድር እንረዳለን። አንድ ሰጋጅ ዉዱእ ማጥፋቱን እርግጠኛ እስካልሆነ ድረስ በዉዱኡ ላይ እንደፀና ይቆያል።