ተረከዞቻችሁን ከእሳት አድኑ! ዉዱእን አዳርሳችሁ አድርጉ!

ተረከዞቻችሁን ከእሳት አድኑ! ዉዱእን አዳርሳችሁ አድርጉ!

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ከመካ ወደ መዲና ተመለስን። ውሃ የሚገኝበት መንገድ ላይ የደረስን ጊዜ ሰዎች ዐስርን በወቅቱ ለመስገድ በመቻኮል ፈጥነው ዉዱእ አደረጉ። ወደነርሱም ተረከዞቻቸው ውሃ ያልነካው ግልፅ ሆኖ ደረስንባቸው። በዚህ ወቅትም የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ " ተረከዞቻችሁን ከእሳት አድኑ! ዉዱእን አዳርሳችሁ አድርጉ!"»

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው ከመካ ወደ መዲና እየተጓዙ ሳለ መንገዳቸው ላይ ውሃ አገኙ። ከፊል ሶሐቦችም ዐስርን ለመስገድ ዉዱእ በማድረግ ተቻኮሉ። ከመቻኮላቸውም የተነሳ ተረከዞቻቸው ደረቅ እንደሆነና ውሃ እንዳልነካው ለተመልካችም በግልፅ ያስታውቅ ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ በሚያደርጉ ወቅት የእግራቸውን ተረከዝ ከመታጠብ ችላ ለሚሉ ሰዎች የእሳት ውስጥ ቅጣትና ጥፋት እንዳለባቸው ተናገሩ። ዉዱእን አሟልቶ በመፈፀም ላይ ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉም አዘዟቸው።

فوائد الحديث

በዉዱእ ወቅት ሁለት እግሮችን መታጠብ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን። (ከመታጠብ ይልቅ) ማበሱ ብቻ ቢፈቀድ ኖሮ ተረከዙን ማጠብ የተወን ሰው በእሳት አይዝቱበትም ነበርና።

የሚታጠቡ አካላቶችን በትጥበት ማዳረስ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን። ማጠብ ግዴታ ከሆነበት አካል ሆነ ብሎም ይሁን ተዘናግቶ ትንሽ አካል ብትሆን እንኳ የተወ ሰው ሶላቱ ትክክለኛ አይሆንም።

አላዋቂን ማስተማርና ማረም አንገብጋቢ መሆኑን እንረዳለን።

ዐሊም (አዋቂ) የሆነ ሰው ግዴታዎችንም ይሁን ሱናዎችን ትተው ሲያይ ተገቢ በሆነ መልኩ ያወግዛል።

ሙሐመድ ኢስሐቅ አድደህለዊ እንዲህ ብለዋል: ዉዱእን ማዳረስ ሶስት አይነት ነው። ግዴታ: ይህ የዉዱእን ቦታ አንድ ጊዜ ማዳረስ ነው። ሱና: ይህም ሶስት ጊዜ ማጠቡ ነው። ተወዳጅ: ይህም ሶስት ሶስት ጊዜ ከማጠብም ጋር ቦታዎቹን እያረዘመ መታጠብ ነው።

التصنيفات

የዉዹእ አደራረግ