'አንድ ሰውዬ ውዱእ አደረገና እግሩ ላይ ጥፍር የምታክል ስፍራ ተወ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተመለከቱትና እንዲህ አሉት: ‹ተመለስና ዉዱእህን አሳምር!›…

'አንድ ሰውዬ ውዱእ አደረገና እግሩ ላይ ጥፍር የምታክል ስፍራ ተወ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተመለከቱትና እንዲህ አሉት: ‹ተመለስና ዉዱእህን አሳምር!› ተመልሶ (አስተካከለና) ከዚያም ሰገደ።'

ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው: እንዲህ አለ: "ዑመር ቢን አልኸጧብ እንዲህ ብሎ ነገረኝ: 'አንድ ሰውዬ ውዱእ አደረገና እግሩ ላይ ጥፍር የምታክል ስፍራ ተወ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተመለከቱትና እንዲህ አሉት: ‹ተመለስና ዉዱእህን አሳምር!› ተመልሶ (አስተካከለና) ከዚያም ሰገደ።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ዉዱእ አድርጎ የጨረሰን ሰውዬ እግሩ ላይ ጥፍር የምታክል የዉዱእ ውሃ ያልነካት ስፍራን እንደተመለከቱበት ተናገሩ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ተወው ስፍራ እየጠቆሙ እንዲህ አሉት: ተመለስና ዉዱእህን አሳምር! አሟልተህ አድርግ! ለሁሉም አካልህ ከውዱኡ ውሃ የሚገባውን ሐቅ ስጠው አሉት! ሰውዬውም ተመለሰና ዉዱኡን አሟልቶ ሰገደ።

فوائد الحديث

በመልካም ለማዘዝ መፍጠን፣ መሃይማንንና ዝንጉዎችን ማንቃት በተለይ የሚሰራው ውግዝ ስራን ተከትሎ አምልኮ የሚበላሽበት ከሆነ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።

የዉዱእ አካላትን በውሃ ማዳረስ ግዴታ ነው። ከውዱእ አካላት ትንሽ እንኳ ብትሆን የተወሰነን የተወ ሰው ዉዱኡ ትክክል አይደለም። ዉዱእ ያደረገበት ወቅት ከረዘመ ደግሞ መድገም ግዴታው መሆኑን እንረዳለን።

ዉዱኡን ማሳመር የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን። ይህም አሟልቶ በማድረግና በሸሪዓ በታዘዘው መልኩ በማዳረስ ነው።

ሁለት እግሮች ከዉዱእ አካላት መሆናቸውን እንረዳለን። እነርሱን ማበስም በቂ አይደለም። የግድ መታጠብ አለባቸው።

ሁሉንም የዉዱእ አካል ከበስተፊቱ ያለው ከመድረቁ በፊት በሚያጥብበት ልክ በዉዱእ አካላት መካከል ማከታተል ይገባል።

አለማወቅና መርሳት ወንጀለኝነትን እንጂ ግዴታን አያነሱም። ዉዱኡን ያላዳረሰው ይህን ሰውዬ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለማወቁ ምክንያት እንዲደግመው አዘዙት እንጂ ውዱእ የማድረግ ግዴታውን አላነሱለትም።

التصنيفات

የዉዹእ ማዕዘናት, የዉዹእ ማዕዘናት