እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'

እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'

በዑሥማን ነፃ የወጣ የሆነው ሑምራን እንዳስተላለፈው እሱ "ዑሥማንን የውዱእ እቃ እንዲያመጡላቸው ሲጣሩ አየ። (የውዱእ እቃ ሲቀርብላቸውም) ከእቃው ውሀ በእጆቻቸው ላይ አፈሰሱ። እያፈሰሱም ሶስት ጊዜ አጠቧቸውቸው። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን በውዱእ እቃ ውስጥ አስገብተው ውሀ ዘገኑና በዚያው ተጉመጠመጡ አፍንጫቸው ውስጥም ውሀውን አስገብተው ድጋሚ አስወጡ። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ፣ ሁለት እጆቻቸውንም እስከ ክርኖቻቸው ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም ጭንቅላታቸውን አበሱ። ከዚያም ሁለት እግሮቻቸውን ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እንዲህ አሉ 'ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚህ መልኩ ውዱእ ሲያደርጉ ተመልክቻቸዋለሁ። ከዚያም 'እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ዑሥማን (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ እጅግ በጣም የተብራራ እንዲሆን ተግባራዊ በሆነ መንገድ አስተማሩ። በውዱእ እቃ ውሀ እንዲያመጡላቸው ጠየቁ። ቀጥሎም በእጆቻቸው ላይ ሶስት ጊዜ አፈሰሱ። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን እቃ ውስጥ ከተው ውሀ በማውጣት ውሀውን አፉቸው ውስጥ ከተው ካመላለሱ በኋላ ተፉት። ቀጥሎም ውሀውን ወደ አፍንጫቸው ውስጥ ከሳቡ በኋላ መልሰው አወጡት። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እጃቸውን ከክርናቸው ጋር ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እጃቸውን አርጥበው ጭንቅላታቸው ላይ አንድ ጊዜ አበሱ። ከዚያም ሁለት እግሮቻቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው ጋር ሶስት ጊዜ አጠቡ። ዑሥማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ዉዱአቸውን ባጠናቀቁ ጊዜ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መልኩ ዉዱእ ሲያደርጉ እንደተመለከቱና በዚህ መልኩ ዉዱእ አድርጎ ልቡንም ጌታው ዘንድ ጥዶ በተመስጦ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው አላህ በዚህ የተሟላ ዉዱእና የጠራ ሶላት ምክንያት ያለፈውን ወንጀሉ በመማር እንደሚመነዳው እንዳበሰሯቸው ነገሯቸው።

فوائد الحديث

ከእንቅልፍ ተነስቶ እንኳ ባይሆን ዉዱእን ሲጀምር እጁን እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት ሁለት እጆቹን መታጠቡ እንደሚወደድለት እንረዳለን። ከሌሊት እንቅልፍ ነቅቶ ከሆነ ግን እጆቹን ማጠቡ ግዴታ ነው።

አንድ አስተማሪ ተማሪዎቹ ዕውቀቱን የሚገነዘቡበትንና የሚሰርፅበትን ቀላል መንገድ መጠቀም ይገባዋል። ከዚህም መካከል በተግባር ማስተማር ነው።

አንድ ሰጋጅ ከዱንያ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ አዘናጊ ውልታዎችን ማስወገድ ይገባዋል። የተሟላ ሶላት ልብን ሶላቱ ውስጥ በመጣድ ነው የሚገኘው። ያለበለዚያ ከማሰብ ሙሉ ለሙሉ መፅዳት አስቸጋሪ ነው። እሱም ነፍሱን መታገልና ሀሳቡን ሶላቱ ላይ መገደብ ይገባዋል።

ዉዱእ ላይ ቀኝን ማስቀደም እንደሚወደድ፤

በመጉመጥመጥና አፍንጫ ውስጥ ውሀ አስገብቶ በማስወጣት መካከል ቅደም ተከተሉን መጠበቅ የተደነገገ መሆኑን ፤

ፊትን፣ ሁለት እጅንና ሁለት እግርን ሶስት ሶስት ጊዜ መታጠብ እንደሚወደድ እንረዳለን። ግዴታው ግን አንድ ጊዜ ነው።

ላሳለፍነው ወንጀል የአላህን ምህረት ለማግኘት ሁለት ነገሮች መሰባሰባቸውን ተከትሎ ነው የሚገኘው፤ እነሱም ዉዱእ እና ሐዲሡ ላይ በተጠቀሰው መልኩ ሁለት ረከዓ መስገድ ናቸው።

ሁሉም የዉዱእ አካላቶች ክልል አላቸው። የፊት ክልል: በርዝመት ከተለመደው የራስ ፀጉር መብቀያ እስከ ፂም መውረጃና አገጭ ድረስ በጎን ደግሞ ከጆሮ እስከ ጆሮ ነው። የእጅ ክልል ደግሞ: ከጣቶች ጫፍ እስከ ክርን ነው። የጭንቅላት ክልሉ ደግሞ ከተለመደው ፀጉር መብቀያና የፊት ጎኖች እስከ ላይኛው ማጅራት ነው። ሁለት ጆሮዎችን ማበስ ጭንቅላትን ማበስ ውስጥ የሚካተት ነው። የእግር ክልሉ ደግሞ: ሙሉ ተረከዝን በእግሩና በባቱ መካከል ከሚለየው አጥንት ጋር ማጠብ ነው።

التصنيفات

የዉዹእ አደራረግ