ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር።

ዐምር ቢን ዓሚር ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር። 'እናንተስ እንዴት ነበር የምታደርጉት?' አልኩኝ። አነስም 'ዉዱእ እስካላጠፋን ድረስ (የነበረን) ዉዱእ ይበቃን ነበር።' አለ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ ባያጠፉ ራሱ ለሁሉም ግዴታ ሶላቶች ዉዱእ ያደርጉ ነበር። ይህም ተጨማሪ ምንዳና ትሩፋትን ለማግኘት ነው። ዉዱእ እስካለው ድረስ በአንድ ዉዱእ ከአንድ ግዴታ ሶላት በላይ መስገድም ይፈቀድለታል።

فوائد الحديث

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አብዝተው ይሰሩት የነበረው የበለጠ ሙሉ የሆነውን በመፈለግ ለሁሉም ሶላት ዉዱእ ማድረግ ነው።

ለሁሉም ሶላት ዉዱእ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።

በአንድ ዉዱእ ከአንድ ሶላት በላይ መስገድ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።

التصنيفات

የዉዹእ ትሩፋት