ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ…

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዹእ ያደርጉ ነበር።

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዹእ ያደርጉ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአንድ ቁና እስከ አምስት እፍኝ በሚደርስ ውሃ ከጀናባ ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዱእ ያደርጉ ነበር። ቁና ማለት አራት እፍኝ ውሃ ማለት ሲሆን እፍኝ ማለት ደግሞ መካከለኛ ተፈጥሮ ያለው ሰው በሁለቱ መዳፎቹ ሙሉ የሚያክል ነው።

فوائد الحديث

የዉዱእና የትጥበት ውሃ ላይ ቆጣቢ መሆንና ውሃው ትንሽ ቢሆን እንኳ አለማባከን እንደሚገባ እንረዳለን።

የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ ስለሆነ እንደአስፈላጊነቱ የዉዱእና የትጥበት ውሃን ማሳነስ እንደሚወደድ እንረዳለን።

ከዉዱእና ትጥበት የሚፈለገው ሳይሰስቱና ሳያባክኑ አዳቡና ሱናውን ከመጠበቅ ጋር አሟልቶ መፈፀም ነው። ወቅቱን፣ የውሃውን ብዛትና ማነስ የመሳሰሉትን ግምት ውስጥ አስገብቶ ማድረግ ነው።

ጀናባ የሚለው ስም የዘር ፈሳሽ ያፈሰሰ ወይም ግንኙነት የፈፀመ ሁሉ የሚገለፅበት ስም ነው። በዚህም የተሰየመው እስኪፀዳ ድረስ ግለሰቡ ከሶላትና ከአምልኮ ስለሚርቅ ነው።

ቁና: የታወቀ መለኪያ ነው። የተፈለገውም ነቢያዊው ቁና ነው። የሚመዝነውም ጥሩ በሆነ የስንዴ ዘር (480) ግራም የሚመዝን ነው። በሊትር ደግሞ (3 ሊትር) የሚይዝ ነው።

እፍኝ: አንዱ ሸሪዓዊ መስፈሪያ ነው። እርሱም መካከለኛ የሆነ ሰው መዳፍ እጁን ዘርግቶ በሁለት እጁ የሚዘግነውን ያህል ማለት ነው። አንድ እፍኝ በፉቀሃዎች ባጠቃላይ ስምምነት የአንድ ቁና ሩብ ነው። መጠኑም (750) ሚ·ሊ ይመዝናል።

التصنيفات

የዉዹእ ሱናና ስነ-ስርዓት