አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።

አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ትክክለኝነት ከሚያስፈልጉ መስፈርቶች መካከል ጠሀራ አንዱ መሆኑን ገለፁ። ስለሆነም ሶላት መስገድ በፈለገ ሰው ላይ እንደሰገራ ወይም ሽንት ወይም እንቅልፍና መሰል ሌላ ዉዱእ ከሚያፈርሱ ነገሮች መካከል አንድም አፍራሽ ነገር ከተከሰተ ዉዱእ ማድረግ ግዴታው ነው።

فوائد الحديث

ዉዱእ የሌለው ሰው ከትልቁ ሐደሥ በትጥበት፤ ከትንሹ ሐደሥ ደግሞ በዉዱእ እስኪፀዳ ድረስ ሶላቱ ተቀባይነት አይኖረውም።

ዉዱእ ማለት ውሀን አፍ ውስጥ በመያዝ አመላልሶ በመትፋት ከዚያም ውሀን ወደ አፍንጫ ውስጥ መሳብ ከዚያም ማውጣት፤ ቀጥሎ ፊቱን ሶስት ጊዜ ማጠብ፤ ቀጥሎ ሁለት እጆችን ክርንን ጨምሮ ሶስት ጊዜ ማጠብ፤ ቀጥሎ ጭንቅላትን ባጠቃላይ አንድ ጊዜ ማበስ፤ ቀጥሎ ሁለት እግሮችን ከቁርጭምጭሚቱ ጋር ሶስት ጊዜ ማጠብ ነው።

التصنيفات

ዉዹእ