በሁለት መንገጭላዎቹ መካከል እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያሉትን አካላት (ሊጠብቅ) ዋስትና ለገባልኝ እኔም ጀነትን ዋስትና እገባለታለሁ።

በሁለት መንገጭላዎቹ መካከል እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያሉትን አካላት (ሊጠብቅ) ዋስትና ለገባልኝ እኔም ጀነትን ዋስትና እገባለታለሁ።

ከሰህል ቢን ሰዕድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "በሁለት መንገጭላዎቹ መካከል እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያሉትን አካላት (ሊጠብቅ) ዋስትና ለገባልኝ እኔም ጀነትን ዋስትና እገባለታለሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም እነርሱን በሚገባ ከጠበቀ ጀነት የሚገባባቸው የሆኑ ሁለት ጉዳዮችን ተናገሩ። የመጀመርያው፡ የላቀው አሏህን ከሚያስቆጣ ንግግር ምላስን መቆጠብ፤ ሁለተኛው፡ ብልትን ብልግና ከመፈፀም መጠበቅ ነው። ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ወንጀል የሚፈፀምባቸው እነዚህ ሁለቱ አካላት ስለሆኑ ነው።

فوائد الحديث

ምላስንና ብልትን መጠበቅ ጀነት ለመግባት ሰበብ መሆኑን እንረዳላን።

ምላስና ብልት ተለይተው የተጠቀሱበት ምክንያት የሰው ልጅ በዱንያውም ሆነ በአኺራው ለሚመጣበት መከራ ዋነኛ ምንጮች ሁለቱ በመሆናቸው ነው።

التصنيفات

የጀነትና እሳት ባህሪዎች